...

ከጨለማ ብርሃንን የሚያመነጨው ማሽን

ፀረ-ሶላር ፓኔል የተሰኘ አዲስ መሳሪያ (Anti-solar panel) የተሰኘ አዲስ መሳሪያ ከቀዝቃዛ የምሽት ሰማይ ኃይል መሰብሰብእንደሚችል ተነገረ፡፡ በምድር እና በህዋ መካከል ያለውን የሙቀት ልዩነት በመጠቀም እንዲሰራ ለሙከራ የተገነባው የቴክኖሎጂው ሰርቶ ማሳያ አነስተኛ የኤል.ኢ.ዲ አምፖልን ሲያበራ ታይቷል፡፡ የዚህ የምሽት ጀነሬተር በትልቁ በተሰራ ጊዜ ደግሞ የኤሌክትሪክ ኃይል በማይደርስባቸው ቦታዎች ለሚገኙ ቤቶች ሁሉ በምሽት ጊዜ ብርሃንን እንደሚሰጥ እንዲሁም ለሞባይል ስልክ እና ሌሎች የቤት ውስጥ ቁሳቁሶች ኃይል ምንጭነት መዋል እንደሚችል ተመራማሪዎቹ ይናገራሉ፡፡

ይህ አዲሱ የብርሃን ምንጭ የሚሆነው መሳሪያ የሚመራበት ዋናው መርህ የቴርሞኤሌክትሪክ (thermoelectric) ጀነሬተርን አሰራር በመጠቀም ነው፡፡ ይህም ጀነሬተር ኃይል የሚያመነጨው አንደኛው ክፍሉ ከሌላኛው የቀዘቀዘ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ በዚህም መሰረት የዚህ መሳሪያ ወደ ሰማይ የዞረው ክፍሉ የአልሙኒየም ሳህን ሲኖረው ሙቀት እንዳይገባ ለመከለልም ብርሃንን ማሳለፍ በሚችል ሽፋን የተለበደነው፡፡ ይህ የአልሙንየም ሳህን የሚቀበለውን ለዓይን የማይታይ ሙቀት ተሸካሚ ጨረር (Infrared Radiation) በመገደቡ ሳቢያ እንደቀዘቀዘ እንዲቆይም ሆኗል፡፡

የስረኛው የመሳሪያው ክፍል ደግሞ በተደረገለት የአልሙንየም ሳህን በመታገዝ በተከታታይ ከከባቢው አየር ሙቀትን መውሰድ ይችላል፡፡ የጸሃይ ብርሃን በሌለበት በምሽት ጊዜ የሳህኑ የላይኛው ክፍል ከታችኛው ሙቀቱ ይቀንሳል፡፡ የስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲው ኢንጅነር ዊ ሊ እና የስራ ባልደረባዎቻቸው የዚህ መሳሪያ ሰርቶ ማሳያ ሊሆን የሚችልና ርዝመቱ ሃያ ሴንቲ ሜትር የሆነ መሳሪያቸውን በምሽት በማውጣት ሃይል የማመንጨት አቅሙን ለማየት ሞክረው ነበር፡፡ መሳሪያውም አንድ አነስተኛ ኤልኢዲ አምፖልን ማብራት የሚችል ሃያ ሚሊ ዋት የሚሆን ኃይልን በአንድ ካሬ ሜትር ስፋት አመንጭቷል፡፡ እንደ ተመራማሪዎቹ ከሆነ የመሳሪያውን ቀዝቃዛ የአልሙንየም ሳህን በተሻለ ከሙቀት የሚከልል ሽፋን በማድረግ መሳሪያው እስከ 0.5 ዋት ድረስ ኃይል እንዲያመኘጭ ማድረግ ይቻላል፡፡

Post Comments(1)

...
አብረሀም2 months ago

ደስ የሚል ፈጠራ ነዉ

Leave a reply