...

የሁዋዌይ የኢትዮጵያ ሀላፊ በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ተገኝተው በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙርያ ተወያይተዋል

በኢትዮጵያ የሁዋዌይ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ቻርለስ ዲንግ እና የአካውንት ማናጀሯ ወ/ሮ ሰላም አብረሀም በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንቲትዩት ተገኝተው በጋራ ሊሰሩባቸው በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙርያ ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱ መግቢያ ስለ ኢንስቲትዩቱ አጠቃላይ ገፅታ የሴክተር ሞደርናይዜሽን ዳይሬክተር በሆኑት አቶ በረከት ገለፃ የተደረገላቸው ሲሆን ሁለቱ ተቋማት በትብብር ሊሰሩባቸው የሚችሉባቸው ተግባራትም በገለፃው ተካቶ ቀርቧል፡፡

ሁዋዌይ በኢትዮጵያ በተለያዩ ስራዎች ላይ ያለውን ተሳትፎና በተለይም የዳታ ሴንተሮች ግንባታና ለተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተሰጡና በመሰጠት ላይ ያሉ ስልጠናዎችን አቶ ቻርለስ ዲንግ እና ወ/ሮ ሰላም አብረሀም በውይይቱ ወቅት ያብራሩ ሲሆን ከኢንስቲትዩቱ ጋራም ወደፊት በትብብር ለመስራት ያላቸውን ፍቃደኝነት ገልፀዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሙቀት መለኪያ መሳርያ፣ የፊት መሸፈኛ ጭንብል እና ሳኒታይዘሮችን ለመለገስ ቃል ገብተዋል፡፡

የኢንስቲትቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ለተለያዩ ችግሮች ቴክኖሎጂያዊ መፍትሄ የሚሰጡ ስራዎችን ለብዙ ሀገር አቀፍ ተቋማት ሰርቶ ማስረከቡን ለእንግዶቹ አስረድተዋል፡፡ አያይዘውም ሁዋዌይ ግንባር ቀደም የቴክኖሎጂ ኩባንያ ከመሆኑም ባሻገር ለታዳጊ ሀገራት አጋር ሆኖ እየሰራ መሆኑን ገልጸው ከኩባንያው ጋራ ኮቪድ-19ኝን ጨምሮ በኢኖቬሽን ማዕከላት እንዲሁም በዲጂታላይዜሽን ረገድ ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ታልሞ በተቀረፀው የቴክ ፎር ኦል ፕሮጀክት ዙርያና ሌሎችም የትብብር መስኮች ኢንስቲትዩቱ በጋራ መስራት እንደሚፈልግ ተናግረዋል፡፡

 

 

 Post Comments(0)

Leave a reply