...

የመንግስት ተቋማት አሰራር ማዘመን የተቋማትን ብቁነት ያረጋግጣል ተባለ፤

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የአሰራር ስርዓትን የሚያዘምን በይነ መረብን ለህገ-መንግስት አጣሪ ጉባኤ ጽህፈት ቤት ህዳር 18 ቀን 2012 ዓ.ም ባስረከበበት ወቅት የኢኒስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዱካን ደበበ የመንግስት ተቋማት አሰራር ማዘመን የተቋማትን ብቁነት ያረጋግጣል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የአሰራር ስራዓትን ያዘምናል የተባለው ይህ ኬዝ ፍሎዉ ማኔጅመንት ሲስተም በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎች የበለጸገ ሲሆን ማንኛዉም ጉዳዩ የሚመለከተው የመስሪያ ቤቱ ሰራተኛ በቀላል መንገድ በይነመረብ ሳያስፈልገዉ ያለምንም ዉጣ ዉረድ ሚስጥር ሳይባክን ደንበኛዉን ማስተናገድ እንደሚያስችለው የተነገረለት ሲሆን ለጊዜው በአማረኛና ኢንግሊዥኛ ቋንቋም መዘጋጀቱ ተገልፆል፡፡
በርክክቡ ወቅት የህገ-መንግስተ አጣሪ ጉባኤ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ወይሶ እንደገለጹት ጽህፈት ቤታቸው በርካታ የህገመንግስት ፋይሎች ከመላው የሀገሪቱ ክፍል የሚቀርብለት የፍትህ ተቋም እንደመሆኑ መጠን ስራወን በሚያከናውንበት ወቅት በሚስጥር መያዝ ያለባቸው መዝገቦች የሚስጥር መባካን እንዲሁም አንድን መዘገብ ደግሞ የመመልከት አይነት ችግሮች ይገጠሙት እንደነበር አስታውሰዋው፡፡
በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የተሰራውን የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር ሲስተምን አገልግሎት ላይ በማዋል ያጋጠሙ ችግሮችን ከማቅለሉ ባሻገር የተቋሙን ብቁነት በማሳደግ ደንበኞች አገልግሎቱን ካሉበት ሆነው እንዲጠይቁና እንዲከታተሉ የሚያስችል ሲስተመ መሆኑ ለጽህፈት ቤታቸው ፍቱን መፍትሄ እንደሆነም አክለው ገልፀዋል፡፡

አቶ ሳንዱካን በበኩላቸው የህገ-መንግስተ አጣሪ ጉባኤ በኢንስቲትዩቱ የበለፀገውን ይህን የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር ሲስተም አገልግሎት ላይ ለማዋል ያሳዩትን ቁርጠኝነት አድንቀው ቀጣይ ድጋፋቸውም እንደማይለያቸው ገልጸው መሰል የመንግስት ተቋማትን ለማዘመን መንግስት ያስቀመጠውን አቅጣጫ በመገንዘብ ለኢንስቲትዩታቸው ለሚያቀርቡ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ እንደሚሰጥም ተናግረዋል፡፡

 

 

Post Comments(0)

Leave a reply