...

ሁለቱም ዓይኖቻችን እንዴት እኩል ሊንቀሳቀሱ ቻሉ? አስደናቂው ውስጣዊ ስራ

እኛ የሰው ልጆች ልክ እንደ አብዛኛዎቹ እንስሳት ሁለት ዓይኖችን ይዘናል፡፡ ይህ ትልቅ ምክንያት አለው፤ የመጀመሪያው አንዱ ዓይናችንን ብናጣ እንኳን በቀረው ለማየት እንድንችል ሲሆን ሌላኛው ምክንያት ግን ከአደን ጋራ ተያይዞ በየጊዜው እያደገ ለመጣው የእይታ ጥልቀታችን እንዲረዳን ነው፡፡ ሆኖም ፍፁም እኩል በሆነ አኳኃን በጋራ ካልተንቀሳቀሱ የሁለት ዓይኖች መኖር ሁለት የተለያየ ምስልን እንድናይ በማድረግ ችግር ሊሆንብን ይችላል፡፡

ታድያ አካላችን እንዴት ይህን ሊያደርግ ተቻለው?

የሁለት ምስል እይታን ለመግታት አዕምሮአችን ሁለት የግብረ መልስ ስርዓቶችን ይጠቀማል፤ በዚህም ሁለቱንም ዓይኖችቻንን የሚቆጣጠሩት ጡንቻዎችን ርዝማኔ እጅግ በተመሳሳይ ቅኝት በማስኬድ በሚያስደንቅ ሁኔታ ፍፁም ተመሳሳይነት ያለው የሁለት ዓይኖች እንቅስቃሴን ይፈጥራል፡፡

እያንዳንዱ ዓይኖችቻን እንቅስቃሴያቸውን የሚቆጣጠሩላቸው ስድስት ስድስት ጡንቻዎች ሲኖሯቸው ሁለቱ አይኖቻችን እኩል ይንቀሳቀሱ ዘንድ አስራ ሁለቱም ጡንቻዎች በፍፁም ተግባቦት መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው የዛሬ 15 ዓመት ገደማ በካናዳ ሜዲካል አሶሴሽን ጆርናል ላይ የወጣ ጥናት አረጋግጦ ነበር፡፡ እንደ አይን ህክምና ባለሙያው ዶ/ር ዴቪድ ጋይቶን ከሆነ አዕምሮአችን በአስገራሚ ሁኔታ የተደራጀው የነርቭ ስርዓቱ 12 ቱንጡንቻዎች በሚፈለገው አቅጣጫ ለማማተር ምን ያህል ግፊት እንደሚያስፈልጋቸው በየጊዜው እየተረዳ ይሄዳል፡፡

ይህ ቀመር ይዘነው የምንወለደው ሳይሆን ኋላ ላይ የምናገኘው ነው፡፡ የህፃናት አዕምሮ ይህን ቀመር በበቂ ሁኔታ እስከሚለምድ ከሶስት እስከ አራት ወራት ይፈጅበታል፡፡ ታድያ እድሜያችን ሰማንያዎቹ ውስጥ እስከሚገባ ድረስ ይህ ችሎታ ሳይለየን ቆይቶ የኋላ ኋላ ይከዳንና ከእጃችን መውጣት ይጀምራል፡፡

ከግብረ መልስ የመማር ሂደቱ ጅማሬ ጡንቻዎቻችን አቅጣጫቸውን ከሚስቱበት ቅፅበት አንስቶ ይሆናል፡፡ ይህ ደግሞ ትናንት ዛሬም ሆነ ወደፊት የሚከለሰት ነው፤ ይህም አልፎ አልፎ ሁለት እይታን ሲያስከትልብን ይስተዋላል፡፡ አንዳንዴ ይህ የሚከሰትበት ምክንያት የተወሰኑ ጡንቻዎች ከአጋሮቻቸው ረዘም ብለው ስለሚገኙ ሊሆን ይችላል፡፡

እነዚህ የአይን ውስጥ ክስተቶች በብዛት የሚከሰቱ ሆነው ሳለ ተፅዕኖአቸው አነስተኛ በመሆኑ ብቻ ልናስተውላቸው አንችልም፤ አዕምሮአችን ግን ያስተውላቸዋል፡፡ በማስተዋል ብቻም አይቀርም፤ ስህተቶችን ለማስተካከል ይጥራል፡፡ ከአንድ ሴኮንድ ባነሰ ጊዜ ውስጥ አዕምሮአችን ሁለቱን ዓይኖቻችንን በተቃራኒ አቅጣጫ በማንቀሳቀስ መልሶ አንድ ያደርጋቸዋል፡፡ በተቃራኒው ሁለቱም አይኖች ከነ ስህተታቸው በዚያው በተመሳሳይ አቅጣጫ እንቅስቃሴያቸውን ቢቀጥሉ ግን ስህተቱን ከሌላኛው አይን አንፃር ማስተካከል ሳይችሉ ቀርተው ስርዓቱ የሚበላሽ ይሆናል ሲሉ ዶ/ር ዴቪድ ያስረዳሉ፡፡

ዳግም በማዋቀሩ ሂደት ውስጥ የሰበሰበው መረጃ አዕምሮአችን የዓይን እንቅስቃሴን የሚቆጣጠሩ ጡንቻዎችን በአንድ ቅኝት ውስጥ ለማዋቀር ይጠቀምበታል፡፡ ለምሳሌ አንዱ ጡንቻ ይበልጥ ፈጥኖ አድጎ ካገኘው አዕምሮአችን ወዲያው ካርታ በመሳል፤ ቀጥሎም ነጠላ የግንባታ ብሎኬቶችን ወደ ጡንቻዎቹ በመሰድደድ በሳምንታት አልያም ወራት ውስጥ ከሌሎቹ ጡንቻዎች ጋራ በቁመት እንዲመሳሰል ያደርገዋል፡፡ ሌላው አካላችን ይህን የአዕምሮአችንን ካርታ እንዴት አድርጎ ወደራሱ በመተርጎም ጡንቻዎችን እንደሚቀይርበት ግን እስካሁንም አይታወቅም፡፡ ሆኖም አዕምሮአችን በግብረ መልስ ሂደት ውስጥ ፍፁም የተመሳሰለ የሁለት ዓይን እንቅስቃሴን ለመፍጠር አፍታም ሸብረክ ሳይል በተጠንቀቅ እንደሚቆም የታወቀ ነው፡፡ እንዲያውም የጡንቻዎቹ ርዝመት በየጊዜው በመስተካከሉ ሳብያ በውስጣቸው የሚገኙ ብዙዎቹ ፕሮቲኖች ዕድሜ ከአንድ ወር አይበልጥም፡፡

ምንጭ፡ Live Science

 

 

 Post Comments(0)

Leave a reply