...

በኢኒስቲትዩቱ የበለፀገው የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጄንሲ የመረጃ አስተዳዳር ስርዓት በይፋ ተመረቀ

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጄንሲ ጋር በመተባባበር ያዘጋጁት የአውቶሜሽን መተግበሪ እና የኦንላይን ትምህርት መማሪያ የዲጂታል መረጃ አስተዳደር ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት የተለያዩ ክቡራን እንግዶች እና የመንግስት ተቋማት ሃላፊዎች በተገኙበት የምረቃ ስነ ስርዓት ተካሂዷል፡፡ ረዥም ጊዜ በወሰደው በዚህ የፕሮጀከት ክንውን ላይ የተለያዩ አጋር ተቋማት ስራው በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ትልቅ ምስጋና ያቀረቡት የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አንዱዓለም አድማሴ ሃገራችን በቴክኖሎጂ የታገዝ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በምታደርገው ጥረት ፕሮጀክቱ ትልቅ እገዛ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡

በምረቃ ስነ ስነስርዓቱ ላይ የመከፍቻ ንግግር ያደረጉት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማሪያም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አጠቃላይ የአሰራር ስርዓትን በኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጀ የማዘመን ስራ በሰፊው እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዛሬ የተመረቀው ፕሮጀክትም የእውቅና አሰጣጥ ስርዓት ለማዘመን እና የመረጃ አያያዝ ችግሮችን ለመቅረፍ ትልቅ እገዛ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡ የፕሮጀክቱ ክንውን ሃገራችን የዲጂታል ሊትሬሲ ትግበራን ለማስፋፋት በምታደርገው ጥረት ላይ የራሱ አስተዋፅኦ አንደሚኖረው ያነሱት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በቴክኖሎጂ የደገፈ የአሰራር ስርዓችን እንዲተገበርሩ እና የላቀ ውጤት እንሲያስመዘግቡም ትልቅ እገዛ እንደሚያደረግ ተናግረዋል፡፡

በስነ ስርዓቱ ላይ ስለፕሮጀክቱ የአሰራር ሂደት ሃሳባቸውን የሰጡት የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክትር አቶ ሙሉቀን ቀሬ ሃገራችን በዲጂታል ኢኮኖሜ ለምታደርገው ግስጋሴ እንዲህ ያሉ የአውቶሜሽን ትግበራዎች እንደመስፈንጠሪያ መሆናቸውን ጠቅሰው ከዚህ በኋላም ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ ፕሮጀክቱን በቀዳሚነት ሲመሩ የነበሩት የቀድሞ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክትር አቶ ሳንዶካን ደበበ በበኩላቸውም ስራው ስንጀምረው ከሌሎች አጋር ተቋማት እንደምናደርገው የትብብር ስራ ብቻ ሳይሆን በትምህርቱ ዘርፍ ትልቅ መሰረት የሚጥል ፕሮጀክት መሆኑን እምነን የተሻለ ውጤት እንዲሚጣ ሰፋፊ ስራዎችን ሰርተናል ብለዋል፡፡

ይህ ዌብ ቤዝድ የመረጃ አስተዳዳር ሰርዓት የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት ጥራት ኤጀንሲ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተሰጣቸው ፈቃድ መሰረት ስራቸውን እንዲያከናውኑ ቁጥጥር ለማድረግ፣ የእውቅና ጥያቄዎቸን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለመስጠት እንዲሁም በእያንዳንዱ ተቋም የተመዘገቡ ተማሪዎችን ከመቆጣጠር ጀምሮ ለተለያዩ የትምህርት ተቋማት የጥራት አገልግሎቶችን ኢዲሰጡ ማገዙ ከብዙ ግልጎሎቶቹ መካከል ነው፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ የመጨረሻ መርኃግብር ላይ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብትና ቴክኖሎጂ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ እምዬ ቢተው አንደገለፁት የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳደሪ ሆነው የሃገሪቱን የእድገት ጉዞ እንዲያጠናክሩ በቴክኖሎጂ የታገዙ የአሰራር ስርዓቶች ወሳኛ መሆናቸውን አንስተው ስራዎች ወደመሬት ወርደው ግባቸውን እንዲመቱ ክትትል ቁጥጥር አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

 

 

 Post Comments(0)

Leave a reply