...

ኮቪድ-19ኝን ተከትሎ የበዛው ፅንስ ውስጥ ሞተው የሚወለዱ ህፃናት ምጣኔ

የተለያዩ ጥናቶች እያመላከቱ እንዳሉት በዓለም ዙርያ በማህፀን ውስጥ ሞተው የሚወለዱ ህፃናት ምጣኔ በአሳሳቢ ፍጥነት እያደገ ነው፡፡ እንደ አጥኚዎች ከሆነ በአንዳንድ ሀገራት ነፍሰ ጡር ሴቶች ኮቪድ 19ኝን ተከትለው በመጡ ገደቦች ምክንያት ለወትሮው ሊያገኙት ይገባ የነበረው የጤና ባለሙያ ክትትል ተነፍጓቸዋል፡፡ በዚህ መንስኤነትም ህፃናት ሞተው እንዲወለዱ የሚያደርጉ የጤና እክሎች ተገቢውን ክትትል አላገኙም፡፡ በደቡብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ በስነ ወሊድ ስፔሻሊስት እንደሆኑት ጄን ዋርላንድ አነጋገር “ነፍሰ ጡር ሴቶችን ከኮቪድ 19 ለመከላከል በምናደርገው ጥረት ባልታሰበ ሁኔታ በማህፀን ሞተው የሚወለዱ ህጻናትን ቁጥር አሳድገናል”፡፡

በጉዳዩ ላይ ከተሰሩት ጥናቶች በስፋት የሚልቀውና በኔፓል ውስጥ በሚገኙ ዘጠኝ ሆስፒታሎች ልጅ የወለዱ 20 ሺህ ሴቶችን አካሎ የወጣው ጥናት ከሁለት ሳምንት በፊት በላንሴት ግሎባል ኸልዝ ላይ ታትሞ ወጥቶ ነበር፡፡ ጥናቱ ይፋ ባደረገው ውጤት መሰረት በማህጸን ሞተው የሚወለዱ ህጻናት ቀድሞ ከነበረበት ከ1000 ውልጃዎች 14ቱ በማህጸን ሞቶ መወለድ ምጣኔ የወረርሺኙን ስርጭት ለመገደብ የተጫኑ የእንቅስቃሴ እገዳዎችን ተከትሎ ቁጥሩ በግማሽ በመጨመር ከሚወለዱ 1000 ህፃናት ውስጥ 21ዱ በማህጸን ሞተው እንደሚወለዱ ለማረጋገጥ ችሏል፡፡ ከዚህ የህፃናት በማህፀን ውስጥ ሞቶ የመገኘት ምጣኔ ዕድገት በስፋት የተስተዋለው የእንቅስቃሴ ዕገዳው በተጣለባቸው የመጀመሪያዎቹ አራት ሳምንታት ውስጥ ነበረ፡፡ በዚህ ወቅት ሰዎች ምግብ ለመግዛት ካልሆነና ጥብቅ የጤና ጉዳይ ካላጋጠማቸው በቀር ከቤት ለመውጣት አይፈቀድላቸውም ነበር፡፡

በስዊድን ባለሙያዎች የሚመራው ጥናት እንዳመለከተው ምንም እንኳን በማህጸን ውስጥ ሞተው የሚወለዱ ህፃናት ምጣኔ በከፍተኛ ሁኔታ ቢያሻቅብም አጠቃላይ ቁጥሩ ላይ ግን ለውጦች አልታዩም፡፡ ይህ ግን በተለይ በሆስታል የሚከናወኑ ውልጃዎች ቀድሞ በሳምንት ከነበሩበት የአማካኝ 1261 ውልጃ በግማሽ በማሽቆልቆል ወደ 651 ዝቅ ከማለቱ ጋራ የተያያዘ ነው፡፡ በወቅቱ ሆስፒታል ውስጥ ሲደረጉ ከነበሩት ውልጃዎች መካከልም ሰፊውን እጅ የያዙት ውስብስብ የሆኑ ውልጃዎች ነበሩ፡፡ በዚህም ምክንያት ከሆስፒታል ውጭ የወለዱ እናቶችም ሆነ ልጆቻቸው ምን እንዳጋጠማቸው መረዳት ባለመቻላቸው ሳብያ ከአጠቃላዩ የነፍሰጡሮች ቁጥር ውስጥ ምን በማህፀን ውስጥ የሞቱ ህፃናትን እንደወለዱም ሆነ አጠቃላይ ምጣኔው ስለመጨመሩ በእርግጠኝነት እንዳይናገሩ አድርጓቸዋል፡፡

በሆስፒታል ውስጥ ከተደረጉ ውልጃዎች መካከል በማህፀን ውስጥ የሞቱ ህፃናት ውልጃዎች የተከሰቱት ወረርሺኙ እናቶች ላይ በቀጥታ ባመጣባቸው የጤና ጉዳቶች ሳይሆን የጤና ስርአቱን ከማቃወሱ ጋራ በተገናኘ ሊሆን መቻሉን ባለሙያዎቹ ያስረዳሉ፡፡ ምናልባትም የመጓጓዣ ስርኣቱ መስተጓሉን ተከትሎ ነፍሰ ጡር እናቶች የፅንሱን ሁኔታ ለመከታተል ወደ ሆስፒታል መሄድ አለመቻላቸውን አልያም ቀጠሮአቸው መሰረዙን፤ ሌሎች ደግሞ ወረርሺኙን ሽሽት ወደ ሆስፒታሎች ከማቅናት መቆጠባቸውንና ክትትል ካደረጉምነ በይነ መረብ እና የስልክ ግንኙነትን በመጠቀም ብቻ መሆኑን ግምታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡

ከኔፓል ባለፈ ሌሎች የአለም ሀገራትም ተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ እራሳቸውን አግኝተዋል፡፡ በሀገረ እንግሊዝ ለንደን ወስጥ ባለው የቅዱስ ጊዮርጊስ ሆስፒታል የተደረገ ሌላ ጥናት እንዳመላከተው በሆስፒታሉ በሚደረጉ ውልጃዎች ላይ በወርሀ ጥር የነበረው ከ1000 ውልጃዎች 2.38ቱ ሞቶ የመወለድ ምጣኔ ከየካቲት እስከ ሰኔ ባሉት ወራት ውስጥ ወደ 9.31 ማደጉን አመላክቷል፡፡ ይህም እንደ ባለሙያዎቹ ከሆነ እናቶች በወረርሺኙ አመጣሽ ምክንያቶች አማካኝነት ወደ በሆስፒታል መጥተው የህክምና ክትትል ባለማድረጋቸው ወይም የጤና እክሎች ሲባባሱ ብቻ ወደ ሆስፒታል በማቅናታቸው መነሻነት ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ በህንድ እና ስኮትላንድም ይህ ሁኔታ ታይቷል፡፡

የአለም ጤና ድርጅት እናት እና ልጁን ከጉዳት ይጠብቅ ዘንድ ነፍሰ ጡር ሴቶች በእርግዝና ወራቶቻቸው ውስጥ ቢያንስ ለስምንት ጊዜ ክትትል እንዲያደርጉ ይመክራል፡፡ አብዛኛዎቹ በፅንስ ውስጥ ሞተው የመወለድ ችግሮችንም በእርግዝና ወቅት በጎን በመተኛት፣ ማጨስ በማቆም እንዲሁም ለጤና ባለሙያዎች ፅንሱ እንቅስቃሴውን እንደቀነሰ በማሳወቅ መከላከል ይቻላል፡፡ በተለይ በመጨረሻዎቹ ሶስት ወራት ውስጥ በአግባቡ ክትትል ማድረግ እጅግ ጠቃሚ ሲሆን በሌሎቹ ወራት ቢሆንም ግን ሰፍሰ ጡር እናቶቹ እንደ ደም ግፊት እና የልጁን ዕድገት በጤና ባለሙያዎች ይመረመራሉ፡፡

ምንጭ፡ Nature

 

 

 Post Comments(1)

...
dobsonz3 days, 7 hours ago

eMqPBR http://pills2sale.com/ levitra nizagara

Leave a reply