...

ቴክ-ሳይንስ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ተሸላሚ ሆነ

በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ተዘጋጅቶ ለአየር የሚበቃው የቴክ-ሳይንስ የቴሌቪዥን ፕሮግራም የ2020 OFAB Ethiopia chapter annual award ውድድር ላይ የአንደኝነት ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡ ሽልማቱ የተበረከተው ፕሮግራሙ በቴሌቪዥን ስርጭት ዘርፍ በዓመቱ የግብርና ባዮ ቴክኖሎጂ ላይ በሰራቸው የሳይንስ ጋዜጠኝነት ስራዎች ነው፡፡

ውድድሩ ሲዘጋጅ ይህ ለአራተኛ ጊዜው ሲሆን ከቴሌቪዥን በተጨማሪም በህትመት እና ራድዮን ዘርፎች በየዓመቱ አወዳድሮ ሲሸልም ቆይቷል፡፡ ከዚህ በመቀጠልም ቴክ-ሳይንስን ጨምሮ በኢትዮጵያ ያሸነፉት ሦስት ተወዳዳሪዎች በአፍሪካ ደረጃ በሚደረገው መሰል ውድድር ተሳታፊ የሚሆኑ ይሆናል፡፡
ሽልማቱን ያበረከተው OFAB ወይም በሙሉ መጠሪያው Open Forum on Agricultural Biotechnology in Africa በዓለም አቀፉ የግብርና ከብቶች ጥናት ኢንስቲትዩት (ILRI) አማካኝነት የሚዘጋጅ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ በስምንት የአፍሪካ ሀገራት የሚንቀሳቀሰው ፎረሙ በባዮ ቴክኖሎጂ ዙርያ ያሉ ባለ ድርሻ አካላትን በእውቀት እና ልምድ በማስተሳሰር የባዮ ቴክኖሎጂን ትሩፋቶች ለአፍሪካውያን ገበሬ ብሎም ባለሀብቶች ለማቋደስ የሚሰራ ነው፡፡
ቴክ ሳይንስ የቴሌቪዥን ፕሮግራምን ዘውትር ቅዳሜ በ10 ሰዓት በድጋሚ ደግሞ ማክሰኞ በ10 ሰዓት በ MOE TV ያገኙታል
በተጨማሪም የዩትዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ያመለጥዎትን ፕሮግራም እና ሌሎች የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዝግጅቶች ያግኙ>>>https://www.youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg


Post Comments(1)

...
dobsonz3 days, 7 hours ago

y4gHYT http://pills2sale.com/ levitra nizagara

Leave a reply