...

በድምጽ የሚያድነው ሸረሪት

ስለአደን ሲታሰብ ታዳኙን አይቶ ማጥቃት በጣም የተለመደ ነው፡፡ ባለ አስፈሪ ፊቱ ሸረሪት ግን የታዳኙን ድምጽ በመስማት ብቻ ነብሳትን ማደን ተክኖበታል ይለናል ከሳይንስ የዜና መጽሔት ያገኘነው ዘገባ፡፡ ሸረሪቱ ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ድምጾችን መለየት የሚችል ሲሆን ባለዝቅተኛ ድምጽ ነብሳት ግን ለአደን ተመራጭ ናቸው፡፡ 

በአብዛኛው ሸረሪቶች የሚታወቁት ድር በሚባል ወጥመዳቸው ታዳኛቸውን በማጥመድ ሲሆን Deinopis spinosa በመባል የሚታወቀው አስቀያሚ ሸረሪት ግን የማዳመጥ የስሜት ህዋሱን ለማደን ይጠቀማል፡፡ ሸረሪቱ ከላይ ወደ ታች እየወረደ በሁለት እግሮቹ ባለአራት መአዘን ድር ያደራል፡፡ ከዚምያ ከነብሳት አንዱ እየበረረ ሲመጣ ባለው የማዳመጥ ችሎታ ተጠቅሞ መረቡን ወደ ታዳኙ ያስጠጋዋል፡፡ ተመራማሪዎችን ይህ የሸረሪቱ የድሩን ቦታ ቀይሮ ታዳኙን የማጥቃት ብልሀት ሳይሆን አይቀርም ድምጽን ለአደን ይጠቀማል እንዲሉ ያስቻላቸው፡፡

 ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ከአመታት በፊት ሸረሪቶች የመስማት ችሎታ እንዳላቸው እንኳን አይታወቅም ነበር፡፡ አሁን ግን ይላል በኮርኔል ዩኒቨርሲቲ የሴንሰሪ ኢኮሎጂስት የሆነው ስታፍስትሮም “ብዙ የሸረሪት ዝርያዎች በእግራቸው ላይ ባለ ልዩ የሆነ ክፍል አስገራሚ የሆነ የመስማት ችሎታ እንዳላቸው ማረጋገጥ ችለናል፡፡”

በምርምሩ ወቅት ተመራማሪዎቹ በ13 ሸረሪቶች ጭንቅላት ውስጥ በጣም ጥቃቅን ኤሌክትሮዶችን (microelectrodes) አስገብተዋል፡፡ ከዚያም በተለያየ ሞገድ ድምጾችን ለቀቁ፡፡ ይህን ሲያደርጉ የሸረሪቱን የድምጽ ነርቭ ህዋስ እንቅስቃሴ በመከታተል ነው፡፡ ከዚያም በሚገርም ሁኔታ ሸረሪቶቹ በአየር ላይ የሚመጣን ከ100 እስከ 10000 hertz የሚለካ ድምጽን በየሞገዱ መስማት እንደሚችሉ አረጋግጠዋል፡፡ እዚህ ላይ የሰው ልጅ መስማት የሚችለው ከ20 እስከ 20000 hertz ድምጽ መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡

ተመራማሪዎቹ ሸረሪት  የተለያየ ሞገድ ያላቸውን ድምጾች መስማት እንደቻለ ማወቃቸው አስገርሟቸዋል፡፡ ተመራማሪዎቹ ስፒከሮችን በሸረሪቶቹ የተለያየ ክፍል በማድረግ ሙከራዎችን ሲደርጉ ከቆዩ በኋላ ምንም አይነት እይታን ሳይጠቀሙ ታዳኞቻቸውን በማዳመጥ አንደሚጠባበቁ ማረጋገጥ ችለዋል፡፡  

ምንጭ The science news magazine   

 Post Comments(0)

Leave a reply