...

ሚትዮሮች ምንድን ናቸው?

አካባቢያችንን አግልቶ የሚያሳይ ዘመን አፈራሽ ቴክኖሎጂዎችን ማለትም እንደቴሌስኮፕ ያሉ ኢኖቬሽኖችን ሳንጠቀም በአይናችን ብሌን ብቻ የምንታዘባቸው አስገራሚ የተፈጥሮ ውበቶች አሉ፡፡ አልፎ አልፎ ጥርት ባለ ጨለማ ሰማይ ላይ አተኩረን በምንመለከትበት ሰአት አብዛኛውን ጊዜ በጣም በፍጥነት የሚያልፉ ደማቅ ብርሀን ያላቸው ነገሮችን ልንመለከት እንችላለን። በተለምዶም ተወርዋሪ ኮከብ ብለን እንጠራቸዋለን (meteors) ወይም ሚትዮሮችን። ተወርዋሪ ኮከቦች በህዋ ውስጥ የሚንሳፈፉ አለቶች ናቸው። ይህ አለት በብዛት የያዘው የብረት መአድን ሲሆን የአለቱ ስፋት ከ 1 ሳ.ሜ (ማይክሮ ሚትዮራይድ) እስከ 1 ሜትር ሊደርስ ይችላል።
ሚትዮሮች ከዋክብት እድሜያቸውን ጨርሰው በሚፈነዱበት ሰአት የፍንዳታቸው ቅሪተ አካል በህዋ ውስጥ ለብዙ ሚሊዮን አመታት ይንሳፈፋል። ተወርዋሪ ኮከቦችም እነዚህ ቅሪተ አካላት ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ይታሰባል። ከዚህ ባለፈ ደግሞ በተለያዩ የህዋ አካላት መካከል በሚከሰት የእርስ በእርስ ግጭት የሚፈጠሩ ፍንጣሪዎች እንደሚሆኑም ይገለፃል።
ተወርዋሪ ኮዋክብት በህዋ ላይ በመንሳፈፍ ላይ ሳሉ ወደምድር ከባቢ አየር መጠጋታቸው አይቀርም። በዚን ግዜ በምድር የስበት ሀይል ይሳባሉ፤ በዚህም ከአየር ጋር በሚያደርጉት ሰበቃ ይቃጠላሉ። ሲንሳፈፍ የነበረውን የህዋ አካል ሚትዮሮይድ የሚል ስያሜ ሲኖረው በሰበቃ ሀይል የተቃጠለውን ሚትዮር ሳይተን ምድር ከደረሰ ሚትዮራይት ተብሎ ይጠራል። ተወርዋሪ ከዋክብት በሰኮንድ 20 ኪሎሜትር ይጓዛሉ። አንዳንድ ጊዜ በጅምላ ሲከሰቱ የሚትዮራይት ሻወር ተብሎ ይጠራል።
Airtable Universe


Post Comments(0)

Leave a reply