...

ዲጂታል ማርኬቲንግ ላይ ያተኮረ ስልጠና በኢንስቲትዩቱ መሰጠት ተጀመረ

የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት በሀገራችን የሚገኙ ስታርትአፖችን በዲጂታል ማርኬቲንግ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙርያ ግንዛቤን ለማስጨበጥ ያለመ ስልጠና ዛሬ መስጠት ጀምሯል፡፡ የሁለት ቀናት ቆይታ የሚኖረው ይህ ስልጠና በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ተሳታፊ የሚሆኑበት ነው፡፡ በፌደራል የስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ውስጥ የICT ዳይሬክተሩ  አቶ ተክሊት በርሄ በስልጠናው ጅማሮ ላይ ለተሳታፊዎች ባሰሙት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር  ኢንስቲትዩቱ ስታርታፖችን በማገዝ ረገድ እያከናወነ ላለው ተግባር አድናቆታቸውን ቸረዋል፡፡ ዲጂታል ማርኬቲንግ ቀድሞ ይሰራበት የነበረውን የገበያ አካሄድ በመቀየር ከICT ጋራ የተሳሰረ እንዲሆን ማድረጉን የተናገሩር አቶ ተክሊት ይህ ስልጠናም ተሳታፊዎችን በጠቃሚ እውቀት፣ ክህሎት እና ደጋፊ የሆኑ መንገዶች ላይ ግንዛቤን የሚሰጥ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በዛሬው መርሀ ግብር ጅማሮ ላይ ስለ በይነ መረብ ወይም ኢንተርኔት ልዩ ልዩ ግንዛቤዎችን የሚያስጨብጥ ስልጠና በኢንስቲትዩቱ ባልደረባ አቶ ገብሬ ኩንታኖ የተሰጠ ሲሆን ይህም በይነ መረብ ምንድነው፣ እንዴት ይሰራል፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ያሳየው እድገት እና ሌሎች መሰል ጉዳዮች ተነስተው ማብራርያ ተሰጥቶባቸው ነበር፡፡ በተጨማሪም ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች የተሰነዘሩ ሲሆን አቶ ገብሬም ሙያዊ ምላሻቸውን ሰጥተውባቸው አልፈዋል፡፡ ከዚህ ባሻገር ግን ዛሬን ጨምሮ ስልጠናው በሚካሄድባቸው በሁለቱም ቀናት ውስጥ ሌሎችም ከዲጂታል ማርኬቲንግ እና አጠቃቀሙ ጋራ የተያያዙ ልዩ ልዩ ርዕሳነ ጉዳዮች ላይ በኢንስቲትዩቱ ተመራማሪዎች እንዲሁም የስልጠናው ተሳታፊዎች አማካኝነት ዳሰሳ የሚደረግባቸው ይሆናል፡፡ ከነዚህ አብይ ጉዳዮች መካከል ድረ-ገፅ፣ መሰረታዊ የዲጂታል ማርኬቲንግ እውቀቶች፣ ብራንዲንግ፣ ፌስቡክ፣ ዩትዩብ እና ሌሎች የማህበራ ሚዲያ ብሎም የበይነ መረብ አማራጮችን ተጠቅሞ ማከናወን በሚቻል የማርኬቲንግ እንቅስቃሴ ላይ ያተኮሩት ይገኙበታል፡፡

በስልጠናው ላይ ከቆዳ፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ ግንባታ፣ ባልትና እና ሌሎችም ዘርፎች ተውጣጡ 37 ኢንተርፕራይዞች ተሳታፊ የሆኑበት ሲሆን እነዚህ ከፌደራል የስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ጋራ በመተባበር የተመረጡ ናቸው፡፡Post Comments(0)

Leave a reply