...

ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው የተሞከረው የሃይፐርሉፕ ቴክኖሎጂ

ሃይፐርሉፕ አዲሱ የትራንስፖርት ቴክኖሎጂ በመሆን አለማችንን የተሻለች ለማድረግ የተወጠነ እጅግ በጣም ፈጣን የትራንስፖርት አማራጭ ነው፡፡ የቴክኖሎጂው አይነት ለረዥም ጊዜ በተለያዩ የምርምር ሂደቶች ያለፈ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ከግልና መንግስታዊ ሙከራዎች ባለፈ ለንግድ የቀረበበት ሁኔታ የለም፡፡

የአሜሪካው ቨርጅን ሃይፐርሉፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ቴክኖሎጂውን በሰዎች ላይ የሞከር ድርጅት ሲሆን ምስረታውን ካደረገበት 2014 እንስቶ የተለያዩ ሙከራዎችን በቴክኖሎጂው ዙሪያ ሲያደርግ የቆየ ነው፡፡ ሙከራው ከላስ ቬጋስ ወጣ ባለ የበረሃ ቦታ የተካሄደ ሲሆን ኩባንያው በሰራው 500 ሜትር በሚጠጋ እንደሃዲድ በሚዘረጋ የቫኪዩም ትዩብ እና የመንገደኞች ፖድ አማካኝነት የተከናወነ ነው፡፡ የቫኪዩም ትዩብ አገልግሎት እንደባቡር ሃዲድ እጅግ በፍጥነት የሚጓዘውን የመንገደኞች መያዣ ፖድ የማሳለጥ ስራ ሲሆን ሌሎች የኤሌክትሪክ ማራዘሚያ መሳሪየዎች እና ኤሌክትሮ ማግኔቲክ መወጣጫዎች የቴክኖሎጂው ተጨማሪ አካላት ናቸው ፡፡

በትራንስፖርት ኢንዱስትሪው በጣም ፈጣን ከሚባሉት የኤሌክትሪክ ባቡሮችና በራሪ አውሮፕላኖች በላይ እጅግ ፈጣን ወይም (ultra-fast speeds) የሚባልለት እና ለዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚኖረው የሃይፐርሉፕ ቴክኖሎጂ ጥንስሱ ከዛሬ 90 አመት በፊት ቢሆንም መንገደኞቹን ይዞ የመጀመሪያው ሙከራውን ያደረገው በፈረንጆቹ 2020 ነው፡፡ ኩባንያው ቴክኖሎጂውን ለመሰራት በሚጀመርብት ግዜ 600 ማይልስ በሰዓት ሊጓዝ የሚችል ሃይፐርሉፕ ለመስራት ያለመ ሲሆን ይህም ከኒው ዮርክ ከተማ እስከ ዋሽንግተን ዲስ ያለውን ርቀት በ30 ደቂቃ የሚያጠናቅቅ ነው፡፡ የቨርጅን ግሩፕ ዋና መሰራች ሪቻርድ ብራንሰን ስለቴክኖሎጂውና ስለተሳካው ሙከራ እንደሚናገሩት በመጪዎቹ ጊዚያት የሰዎችን አጠቃላይ ህይወት መቀየር የሚያስችል ኢኖቬሽን ከመሆኑም በላይ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ትልቅ የመሰርት ድንጋይ የሚያስቀምጥ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

ቨርጅን ግሩፕ ቴክኖሎጂውን በመንገደኞች ላይ የሞከረ የመጀመሪው ድርጅት ቢሆንም በሃይፐርሉፕ ዘርፍ ላይ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን የሚያደርጉ የተለያዩ ኩበንያዎች አሉ፡፡ ለአብነት በሎስ አንጀለስ መቀመጫውን ያደረገው ሃይፐርሉፕ የትራንስፖርት ቴክኖሎጂ በተባበሩት የአረብ ኢሜሬትስ፣ በፈረንሳይ እና በጀርመን የተለያዩ የሙከራ ፕሮጀክቶችን በመካሄድ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ እንደአውሮፓውያኑ በ2022 የመጀመሪያውን የንግድ ሃይፐርሉፕ ትራንስፖርት ለማቅረብም በዝግጅት ላይ ነው፡፡

ይህ የትራንስፖርት ቴክኖሎጂ ከደህንነትና ከፍጥነት አንጻር እጅግ የላቀ ቢሆንም ከሚፈልገው የወጪ ምጣኔ አኳያ እና ከሚወስደው የመንገድ መሰረተ ልማት አኳያ በቀላሉ ለመተግበር የሚያስቸግር ቴከኖሎጂ መሆኑን ብዙዎች ይገልፃሉ፡፡ ምንጭ፡ Big ThinkPost Comments(0)

Leave a reply