...

አዲሱ ብርሀንን መሰረት ያደረገው ኳንተም ኮምፒውተር

በቻይና የሚገኙ የኮምፒውተር ሳይንስ ተመራማሪዎች እስካሁን በአለማችን ውስጥ ባሉ ኮምፒውተሮች መከናወን የማይችሉ ስሌቶችን የሚያከናውን photonic quantum computer የተሰኘ በብርሀን ቅንጣቶች የሚታገዝ ኮምፒውተር መስራታቸውን በታህሳስ 3 ለ science news magazine ተናገሩ፡፡ ከዚህ በፊት የዚህ አይነት ብቃት ያለው ምጡቅ ኮምፒውተር በ2019 የጎግል ካምፓኒ ንብረት የሆነው ኳንተም ኮምፒውተር ሲሆን ከፍተኛ የሆነ አስተላላፊ ቁስን የሚጠቀም ነበር፡፡

በቴክሳስ አውስቲን የኮምፒውተር ሳይንስ ተመራማሪ የሆነው Scott Aaronson ይህ ኮምፒውተር ከጎግሉ ኮምፒውተር በኋላ የኳንተም ልእልናን (quantum supremacy) የተጎናጸፈ ብቸኛው ኮምፒውተር ነው ሲል ተናግሯል፡፡ ይህ ኳንተም ኮምፒውተር ፈጣን ባልሆኑ መደበኛ ኮምፒውተሮች (classical computer) ግማሽ ቢሊዮን አመታት የሚጨርስን አንድን ተግባር በ200 ሴኮንዶች ማከናወን ይችላል፡፡ በጣሊያን ሮም ያለው የኳንተም ፊዚክስ ሊቁ Fabio Sciarrino የመጀመሪያ ግብረ መልሴ ‘wow’ ነበር ሲል ተናግሯል፡፡

የጎግል ካምፓኒ የሆነው Sycamore የተሰኘው ምጡቅ ኮምፒውተር ከፍተኛ አስተላላፊ የሆነን እና ሀይልን ያለ ሬዚስተር ማስተላለፍ የሚችል ኳንተም ቁስ መሰረት ያደረገ ነው፡፡ በንጽጽር Jiuzhang (ጥንታዊ የቻይና ሒሳባዊ ጽሁፍ ስያሜ ነው) የተሰኘው አዲሱ የቻይና ኮምፒውተር ውስብስብ የሆነ ኤሌክትሮ መግነጢሳዊ ጨረር ማስተላለፍ የሚችል የብርሀን ህብር የያዘ ነው፡፡ ይህም በመቶወች የሚቆጠሩ አንጸባራቂዎች፣ በርከት ያሉ መስታወቶችና 100 የሚጠጉ  ኤሌክትሮ መግነጢሳዊ ጨረር አነፍናፊዎችን ያካተተ ነው፡፡

Boson sampling በተሰኘ ሂደት ይህ ኮምፒውተር በሌሎች ኮምፒውተሮች የማይከወኑ ተግባራትን ማከናወን ይችላል፡፡ ኮምፒውተሩ ይህንን (Boson sampling) ሂደት ብቻ የሚያከናውን መሆኑ እንደ እጥረት ተወስዶበታል፡፡ የጎግሉ ኳንተም ኮምፒውተር ግን ሌሎች ተግባራትንም ማከናወን ይችላል፡፡

ምንጭ Science news magazinePost Comments(0)

Leave a reply