...

መሬት ከሚልኪ ዌይ ጋላክሲ የመሀለኛ ክፍል (supermassive black hole) 25,800 የብርሃን አመት እንደምትርቅ አንድ ጥናት አመለከተ

የአለም አቀፉ የአስትሮኖሚካል ህብረት እንደአውሮፓውያኑ በ1985 በይፋ የበየነው መረጃ እንደሚያመለክተው መሬት ከሚልኪ ዌይ ጋላክሲ (ረጨት) የመሀለኛ ክፍል 27,700 የብርሃን ዓመት እንደምትርቅ እና በሰኮንድ 220 ኪሎ ሜትሮችን በመጓዝ የጋላክቲክ ማእከሉን (Galactic Center) በዚህ ፍጥነት እንደምትዞር የሚያሳይ ነበር፡፡ ይሁንና ከ15 አመት በላይ የፈጀው አዲሱ የጃፓን የሬዲዮ አስትሮኖሚ ፕሮጀክት ጥናት ይህን ብያኔ የሚያስቀይር ይመስላል፡፡

መኖሪያችን ምድር ቀድሞ ሲታሰብ ከነበረው ይልቅ ከሚልኪ ዌይ ጋላክሲ የመሀለኛ ክፍል ይበልጥ የቀረበች መሆኑን እና በ በሰኮንድ 227 ኪሎ ሜትሮችን በመገስገስ የጋላክሲውን የማሀለኛ ክፍል በ25,800 የብርሃን አመት ርቀት እንደምትዞር በጃፓን የተሰረው አዲስ ጥናት ይፋ አድርጓል፡፡ በተመራማሪዎች ጥቅም ላይ የዋለው የሬዲዮ አስትሮኖሚ ፕሮጀክት አዲስ ምልከታን በማከል ምድር ለጋላክሲው የማሀለኛ ክፍል ያላትን ርቅት በዚህ መልኩ ሲያስቀምጠው የጋለክሲውን ገፅታዎች (modeling of the galaxy) በሚገባ ለመረዳት ተጠቀመበት እንጂ ምድር ላይ የተለየ ተጽዕኖ ይኖረዋል ማለት እንደማይሆን አጥኝዎቹ አስረድተዋል፡፡

አዲሱ የምርምር ውጤት እስካዛሬ ከነበሩት ግኝቶች ይልቅ ተሻሻሎ የቀረበ ሲሆን በጃፓን የሬዲዮ አስትሮኖሚ ፕሮጀክት ለ15 ዓመታት በተሰበሰበ የሚልኪ ዌይ ጋላክሲ የ3-D መዋቅር እና ሌሎች የፍጥነትና ስፓሻል ገፅታዎች ላይ በተደረገ አሰሳ ነው፡፡ VERA በሚል የተያዘው ይህ የምርምር ፕሮጀክት Very Long Baseline Interferometry (VLBI) የተሰኘ የአስትሮኖሚ የትንተና እና የአሰሳ ቴክኒክ ስለመከተሉ የሚናገሩት ተመራማሪዎች ይህን ቴክኒክ በመጠቀምም ከጃፓን አብዛኞቹ ደሴቶች የተወሰዱ የራዲዮ ቴሌስኮፕ መረጃዎችን ተቀምሮ መሰራቱን ይናገራሉ፡፡

የጥናቱ ውጤት በጋላክሲው ዙሪያ ሊኖር የሚችለውን የህዋ አካላት የቦታ አያያዝ እና የፍጥነት መጠን የሚጠቁም የማሳያ ወይም (simulation) ካርታ ይፋ ማድረግ ሲሆን ይህን በመጠቀምም ሁሉም የህዋ አካላት ከጋላክሲው የመሀለኛ ክፍል በምን ያህል ርቀት እንደሚገኙ እና በምን ያህል ፍጥንት እንደሚጓዙ ለመጠቆም የሚያስችል ነው፡፡

ተመራማሪዎች በዚህ የሲሚዩሌሽን ካርታ ለማረጋገጥ እንደቻሉትም እስከዛሬ የሚታሰበው የምድር የፍጥነት ወሰን እና ከጋላክቲክ ማእከሉ የምትርቅብት መጠን በ7 ኪሎሜትር እና በ2,000 የብርሃን አመት ቀንሶ መገኘቱን ይፋ አድርገዋል፡፡ በጥናታቸው ውጤት መሰረት ትክክለኛው የመሬት የፍጥነት ወሰን በሰኮንድ 227 ኪሎ ሜትሮች ሲያካልል ከጋላክቲክ ማእከሉ የምትርቅብት መጠን ደግሞ 25,800 የብርሃን አመት እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡

*የሚልኪ ዌይ ጋላክሲ የመሀለኛ ክፍል በየትኛውም ጋክሲዎች መካከል የሚገኘው የሱፐርማሲቭ ፀሊም ጉድጓድ ተብሎ የሚጠራው ጥልቁ የህዋ አካል ሲሆን የብርሃን አመት ስሌት ደግሞ በ9 ትሪሊዩን ኪ.ሜ የሚሰላ ነው። አንድ የብርሃን አመት = 9 ትሪሊዮን ኪሎ ሜትሮች

ምንጭ፡ Bigthink እና Airtable UniversePost Comments(0)

Leave a reply