...

የዓመቱ ምርጥ ታዳጊነት ክብርን የተቀዳጀችው ታዳጊ ተመራማሪ

የ15 ዓመቷ የፈጠራ ባለሙያ በታይም መፅሔት የዓመቱ ምርጥ ታዳጊ ተብላ ተመርጣለች፡፡ ከአሜሪካኗ ኮሎራዶ ግዛት የተገኘችው ጊታንጃሊ ራኦ በተለያዩ ዘርፎች ላይ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ፈጥራለች፡፡ ከነዚክ ፈጠራዎቿ መካከልም፤ በሚጠጣ ውሃ ውስጥ የሚገኝ ሊድን የሚለይ መሳርያ፣ መተግበሪያዎች እንዲሁም የሳይበር ላይ ማጭበርበር የሚለየው የክሮም ኤክስቴንሽን ይገኙበታል፡፡

ሆኖም ምርጫው የተከናወነው አሜሪካን ውስጥ በሚኖሩ አምስት ሺህ ታዳጊዎች መካከል ነው፡፡ ከአምስት ሺዎቹ ታዳጊዎች መካከል አምስቱ እጩዎች ታዋቂው የቴሌቪዥን ሾው አዘጋጅና ኮሜዲያን ትሬቨር ኖዋን ጭምር ባካተተው የወጣቶች ኮሚቴ አማካኝነት ተመርጠዋል፡፡ ጊታንጃሊን ጨምሮ አምስቱም የመጨረሻ ዙር ተወዳዳሪዎች መጪው አርብ ላይ በሚደረግ የቴሌቪዥን ዝግጅት ዕውቅናን የሚያገኙ ይሆናል፡፡

እርሷን የሚመስሉ ተመራማሪዎችን ብዙም እንዳልተመለከተችና የሚያጋጥሟት ተመራማሪዎችም አብዛሀው ወንድ ነጮች መሆናቸውን የምትገልፀው ጊታንጃሊ ህልሟ የራሷ የሆኑ መሳርያዎችን መፍጠር እና የዓለምን ችግሮች መፍታት ብቻም ሳይሆን ሌሎችም በእርሷ ልክ እንዲገኙ ማነሳሳት ጭምር መሆኑን ትናራለች፡፡

ስመጥሩ የታይም መፅሔት የአመቱ ምርጥ ሰው የሚላቸውን ግለሰቦች ከአውሮፓውያኑ 1927 አንስቶ እየመረጠ ክብር ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም የዓመቱ ምርጥ ታዳጊን ሲመርጥ ግን ይህ ለመጀመሪያ ጊዜው ነው፡፡ ታይም ፎር ኪድስ የተሰኘና ለህፃናት የሚስማማ መፅሔትንም የሚያሳትመው ታይም አዲሱ ሽልማቱን የህፃናት የቴሌቪዥን ጣብያ ከሆነው ኒክሎዲየን ጋር በመሆን አዘጋጅቶታል፡፡

ባሳለፍነው ዓመት የ16 ዓመት ታዳጊ የሆነችው ግሪታ ተንበርግን የዓመቱ ምርጥ ነስ ብሎ አከብረዋት ነበር፤ ይህም በከባቢ አየር ተቆርቋሪ ስራዎቿ የምትታወቀው ግሪታን እስከዛሬ ክብሩን ካገኙት መካከል በዕድሜ ትንሻ ግለሰብ አድርጓታል፡፡

ምንጭ፡ The GuardianPost Comments(0)

Leave a reply