...

እርግዝና እና የኮቪድ 19 ክትባት

ምንም እንኳን የሚያጠቡና ነብሰጡር ሴቶች በክትባቱ ሙከራ ጊዜ ባይሳተፉም የመረጃ ምንጫችን ላይቭ ሳይንስ ከሙያተኞች አገኘሁት ያለው መረጃ ክትባቱ በሚያጠቡ እናቶችና በነብሰጡሮች ላይ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል ሲል ዘግቧል፡፡ በጉዳዩ ላይ መረጃ የሰጡትን ዶክተር ስቴፋኔ ጋው ጠቅሶ የዘገበው የመረጃ ምንጫችን በጉዳዩ ያለው ትልቁ ጉዳት ሳይንሳዊ የሆነ መረጃ አለመኖሩ ነው ሲል አስነብቧል፡፡ ለዚህም እስካሁን እውቅና በተሰጣቸው ሁለቱ የፊዘርና የሞደርና መድሀኒቶች በሰውነት ውስጥ የሚሰባበርና የሚሰራጭ ኢንፌክሽን የማያስከትል mRNA የተሰኘ ሞሎኪዩል የያዙ መሆናቸውን ዶክተሯ ተናግረዋል፡፡

በጥቅሉ ሲታይ ለነብሰጡሮች የሚሰጡ መድሀኒቶች በሙከራ ወቅት መደበኛ የሆነ ክሊኒካዊ ሙካራ በነብሰጡሮች የማይደረግባቸው መሆኑን 2014 የወጣ የአለም ጤና ድጅት መረጃ ያመለክታል፡፡ ይሁን እንጂ መረጃዎች ቀጥታ ባልሆነ መንገድ በእንስሳትና በሌሎች ምልከታዎች ተሰብስበው የትርፍና ኪሳራ ስሌት እንደሚሰራ ይነገራል፡፡

ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ እርግዝና በኮቪድ 19 ምክንያት በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ የመቆየት እድልን ከፍ ያደርጋል፡፡ በዚህም የሚያጠቡ እናቶችና ነብሰጡሮች መድሀኒቱን ከመውሰዳቸው በፊት ከጤና ግልጋሎት ሰጭዎች ጋር በእርግዝና ወይም በማጥባት ወቅት መድሀኒቱን መውሰድ ባለው ጥቅምና ጉዳት ዙሪያ መነጋገር እንዳለባቸውና መድሀኒቱን በመውሰድና ተጨማሪ መረጃ እስከሚገኝ በመጠበቅ ዙሪያ መወሰን ይኖርባቸዋል ተብሏል፡፡ ዶክተሯ አክለውም የተጋላጭነት መጠናቸው ከፍ ያሉ ሰዎች ከመጠበቅ ይልቅ ፈጥነው መድሀኒቱን ቢወስዱ እንደሚሻል ተናግረዋል፡፡

የአሜካን በሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማእከል (CDC) መድሀኒቱን የወሰዱ የሚያጠቡና ነብሰጡር ሴቶችን ለይቶ ክትትል እያደረገ መሆኑን የዘገበው የመረጃ ምንጫችን በቀጣዩ ወር በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ እንደሚኖር አመልክቷል፡፡ መረጃውንም የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማእከል (CDC) እና የምግብና መድሀኒት አስተዳደር (FDA) አሁን ላይ ያሉ የመረጃ መሰብሰቢያ መንገዶችን በመጠቀም እንደሚሰበስቡ ተነግሯል፡፡

ባጠቃላይ ለላይቭ ሳይንስ መረጃ የሰጡት ዶክተር በአብዛኛው ጥቅም ላይ የዋሉ ክትባቶች በእርግዝና ላይ የከፋ ጉዳት የማያደርሱ መሆናቸውን ቢናገሩም ስሞልፎክስ፣ MMR የተሰኙ ደካማ የሆኑ ቫይረሶችን የተሸከሙ ክትባቶች ለነብሰጡሮችና ለአጥቢዎች የማይሰጡ መሆናቸው መዘንጋት እንደሌለበት አሳስበዋል፡፡

እንደ ምክረ ሀሳብ ዶክተሯ አጥቢና ነብሰጡር እናቶች ሌሎች ሰዎች ከሚወስዱት መጠን ያነሰ ክትባት ቢወስዱ የተሻለ መሆኑን ሲገልጹ አስተማማኝ የሚሆነው ግን ተገቢ የሆነ ክሊኒካዊ ሙከራ መደረጉ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ Live sciencePost Comments(0)

Leave a reply