...

የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከልሳን ቴክኖሎጂ ጋራ በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ

የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከልሳን ቴክኖሎጂ ጋራ በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ፡፡ የቴክኖሎጂ ሽግግርን በዋና አላማነት አንግቦ የተካሄደው የመግባብያ ስምምነቱ በሁለቱም ተቋማት ያሉ ተመራማሪዎችን በማስተባበር የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ውጤት እንደሚያስገኝም ታምኖበታል፡፡ ስምምነቱን በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት በኩል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሙሉቀን ቀሬ ሲፈርሙ ልሳን ቴክኖሎጂን በመወከል ደግሞ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ አዳም ቦዶዊን ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡

ስምምነቱ ሁለቱ አካላት ማሽን ለርኒንግ በመጠቀም የሃገራችንን የተለያዩ ብሄራዊ ቋንቋዎችን ለመተርጎም የሚያስችል ስራዎች ላይ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፍ ላይ እንዲሁም በሁለቱም ተቋማት የሚገኙ ተመራማሪዎች፣ ሶፍትዌር መሀንዲሶች እና ሌሎች ባለሙያዎች በጋራ እንዲሰሩ የሚያደርግ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ልሳን የስልጠና እንዲሁም ቋንቋዎቹን ለመተርጎም የሚያግዝ የማሽን ለርኒንግ ስርዓት እና ኦፕቲካል ካራክተር ሪኮግኒሽን (OCR) ሲስተሞችን ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን ኢንስቲትዩቱም ለጋራ ምርምር የሚያስፈልግ መሰረተልማት፣ ቁሳቁስ እና አስተዳደራዊ አቅርቦቶችን የሚያከናውን ይሆናል፡፡

በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬ ኢንስቲትዩቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በስልጠና፣ ጥናት እና ቢዝነስ መካከል ድልድይ መሆኑንና በሀገሪቱ ስትራቴጂዎች ውስጥም ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት አውስተው ስምምነቱ በፍጥነት ወደ ተግባር እንዲለወጥ ያላቸውን ፍላጎት አንፀባርቀዋል፡፡ አቶ አዳም በበኩላቸው ተቋማቸው በዋናነት መቀመጫውን ጀርመን ሀገር አድርጎ እንደሚሰራ ገልፀው ሀገራዊ ቋንቋዎችን ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን እና በኢትዮጵያ እየሰሩ ያሏቸውን ቴክኖሎጂያዊ ስራዎች አስተዋውቀዋል፡፡Post Comments(0)

Leave a reply