...

የመጀመሪያው አርተፊሻል ልብ በአውሮፓ ለገበያ እንዲውል ፈቃድ አገኘ

 

በአውሮፓ የዘርፉ ተቆጣጣሪዎች የመጀመሪያ የሆነውን ሰው ሰራሽ ልብ ለገበያ እንዲውል ፈቃድ መስጠታቸው ተሰምቷል፡፡ ለሀያ ሰባት አመታት ያክል ሲለፋበት የነበረውና ስኬት አግኝቶ ከሰባት አመታት በፊት ፈቃድ የተሰጠው ሰው ሰራሽ ልብ ለአምራቹ ኬርሜት ትልቅ ተስፋን ሰጥቷል፡፡ ኬርሜት በዘርፉ ስቶክ ገበያ ውስጥ 66 በመቶ ድርሻ ያለው ሲሆን ይህም የገበያ ዋጋውን 407 ሚሊዮን ይሮ አድርሶለታል፡፡

ጅቱ በያዝነው ሳምንት ምርቱን በአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ውስጥ መሸጥ የሚያስችለውን ፈቃድ ማግኘቱን የዘገበው ብሉምበርግ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ይህም በልብ በሽታ እየተሰቃዩ ላሉ ህሙማን የልብ ንቅለ ተከላ ማድረግ የሚያስችላቸውን እድል ይፈጥርላቸዋል ተብሏል፡፡

ሰርጅንና የልብ ቱቦ (heart-valve) ፈጠራ ባለቤት ያደረጉት ስምምነት በፈረንሳይ ሰው ሰራሽ ልብ የሚመረትበትን መንገድ በ1993 ከፍቷል፡፡ የድርጅቱንም ድርሻ ኬርሜትና ኬርፔንቴር የተባሉ ባለቤቶች ይዘውታል፡፡ በመሆኑም የሽያጭ ፈቃዱን በማግኘቱ ኬርሜት የፊታችን ጥር የምርት ሂደቱን እንደሚጀምር አሳውቋል፡፡

ይህ አርቲፍሻል ልብ ተመርቶ ለገበያ ከቀረበ በኋላ ለኬርሜት ከ700 ሚሊዮን ዩሮ በላይ አመታዊ ገቢ እስከ 2030 እንደሚያስገኝለት ተገምቷል፡፡ ምርቱንም በፈረንጆቹ 2021 ሁለተኛ ሩብ አመት ለገበያ እንደሚያቀርብ ድጅቱ አሳውቋል፡፡

ምንጭ Bloomberg Technology

 Post Comments(0)

Leave a reply