...

ሁለቱ የምርምር ተቋማት በጋራ ለመስራት ከስምምነት ደረሱ

የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩትና የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በተቋማዊ የመረጃ አያያዝ ሲስተም ዝርጋታ፣ ዲታ-ቤዝ ወይም በመረጃ አያያዝ ስርአት ግንባታ ብሎም በፖሊሲ ትንተና እና ምርምር ዘዴን ጨምሮ በ12 አባይት ጉዳዮች ላይ በጋራ እንዲሰሩ የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ 

ኢትዮጵያ ከ6 እስከ 7 ቢሊዮን ዶላር በሚደርስ ወጪ ወረዳ ድረስ የዘለቀ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ብታከናውንም ስራ ላይ አለመዋሉን ያወሱት የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ ሁለቱ ተቋማትም ኢንፎርሜሽን እና ኮምዩኒኬሽን ላይ ማዕከል አድርገው በሰው ኃይል ማብቃት ላይ ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ በጥቂት ወራት ውስጥ የትግበራ እቅድ ተዘጋጅቶ በቀጥታ ወደ ስራ መገባት እናዳለበት የተናገሩት ዶ/ር መኩሪያ ኢትዮጵያ ወደ ብልፅግና ለምታደርገው ጉዞም የበኩላችንን ጥረት እንደምናደርግ ተስፋ አለኝ ብለዋል፡፡

የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከእኛ ጋር ለመስራት በመፍቀዱ ደስተኛ ነን ያሉት የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬ ተቋማቸውን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ማብራርያ የሰጡ ሲሆን ወደፊትም በጋራ የተሰሩ ስራዎችን ይዘው ተለቅ ባለ መድረክ እንደሚገናኙ ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል፡፡

ዛሬ ጠዋት በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የተፈረመው ይህ ስምምነት ለሦስት ዓመታት እንዲቆይ የታቀደለት ሲሆን አተገባበሩም በሁለቱ ተቋማት ዋና ዳይሬክተሮች የሚመራ ዓብይ ኮሚቴ አማካኝነት ክትትል ሚደረግበት ይሆናል፡፡Post Comments(0)

Leave a reply