...

የተሳትፎ ጥሪ፤ ለኢኖቬተሮች

የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የኢኖቬሽን ባህልን ለማሳደግና ቀጣይነት ባለው መልኩ ኢኖቬተሮችን ለማፍራት ያግዝ ዘንድ የቅድመ-ኢንኩቤተር ፕሮግራም ተቋሙ አዘጋጅቷል፡፡ በዚህም ፕሮግራም የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች፣ ተመራማሪዎችና ሌሎች ማንኛውም መስፈርቱን የሚያሟሉ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች መሳተፍ የሚችሉበት ሲሆን የስራ ፈጠራ ሃሳባቸውን የሚያሳድጉበት እና ቢዝነስን የሚመሩበት ክህሎትን ይቀስሙበታል፡፡ ከአመልካቾች መካከል ሀያ አምስቱ ተመርጠው ከጥር 19 እስከ  21 2013 ዓ.ም ድረስ በሚካሄደው በዚህ ፕሮግራም ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ መስፈርቱን የምታሟሉ ሁሉ ይህን ሊንክ በመጫን ከዛሬ ታህሳስ 23 2013 አንስቶ እስከ ጥር 7 2013 ድረስ መመዝገብና መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

ለበለጠ መረጃ በኢ-ሜይል አድራሻችን startup@techin.gov.et ወይም አራት ኪሎ (ከፓርላማ ወደ ፒያሳ በሚወስደው ጎዳና) በሚገኘው ዋና ቢሮዋችን በአካል በመገኘት ሊጠይቁን ይችላሉ፡፡

 Post Comments(0)

Leave a reply