...

ባለ ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ካሜራ

ካሜራዎች የሚመለከቱትን ምስል ከማየት ባለፈ የሚረዱ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ምርምር በብሪስቶልና ማንችስተር ዩኒቨርሲቲ ጥምረት መሰራቱ ተነገረ፡፡ በሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች የተሰራው ምርምር ካሜራዎች የሚያዩትን ምስል ምንነት በጥልቀት በመመርመር እንዲረዱት የሚያስችል ነው፡፡ የሮቦቲክስና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ተመራማሪዎች በአሁኑ ወቅት ያሉ ካሜራዎች ምስሎችን ሴንስ የሚያደርጉበት መንገድ ችግር አለበት ብለው ያምናሉ፡፡

እነዚህ ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ካሜራዎቹ ምስልን ለመቅዳት ዲዛይን በተደረጉ የካሜራ ሴንሰሮችና የቪዲዮ ጌሞችን ለማጫወት የሚያገለግሉ የኮምፒውቲንግ ቁሶችን በማጣመር የሚሰሩ በመሆናቸው ሰው ሰራሽ ክህሎት ምስሎችን የሚያገኘው የተለያዩ ቅጅዎች ከሴንሰር ወደ ፕሮሰሰር በሚያደርጉት ጉዞ ነው፡፡

ይህ ሂደት በካሜራችን እይታ ውስጥ አላስፈላጊ ምስሎች እንዲገቡ ያደርጋቸዋል፡፡ ለምሳሌ ራስ-ነድ በሆኑ መኪናዎች ከመንገድ ውጭ ያሉ ለጉዞው የማያስፈልጉ ምስሎች ይገባሉ፡፡ ይህ ምርምርም ያስፈለገው ይህን ችግር ለመቅረፍ ነው፡፡ በሂደቱም አንድን ምስል ሴንስ ማድረግና መረዳትን (learn) በአንድ ጊዜ በማጣመር ለሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚያገለግል ልዩ ካሜራን መፍጠር ተችሏል፡፡

ይህንን ፈጠራ በማበልጸግ ሂደት ውስጥ ተፈጥሯዊ የሆነውን የአይንና የአእምሮን ቅንጅት መሰረት አድርገው እንደሰሩ ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ በኢንጂነሪንግ እና ፊዚካል ሳይንስ ምርምር ካውንስል በሚደገፈው ምርምር የተሰራው ካሜራ ከማሽን ለርኒንግ አቅሙ በተጨማሪ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው በመሆኑ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት እድገት ከፍተኛ አተዋጽኦ እንደሚኖረው ተነግሯል፡፡

ምንጭ፡ SciTechDailyPost Comments(0)

Leave a reply