...

ዳሳሽ ማቴሪያሎች ተግባራዊ የሚሆኑባቸዉ ዘርፍች

ዳሳሽ ማቴሪያል (Sensor material) ማለት የዳሳሽ መዋቅራዊ ዘዴ ያለዉ ሆኖ የአከባቢን ሁኔታ ለምሳሌ የሙቀትን፤ የክብደትን፡ የግፊትን ስሜት ተረድቶ መልስ መስጠት የሚችል ማቴሪያል ነዉ፡፡ የዳሳሽ ማቴሪያል መዋቅር በዉስጡ የብርሀንና የእሳት ሙቀት መለኪያ፡ በሞተር የሚንቀሳቀሱና ኤሌክትሮኒክስን የያዘ ክፍል አለዉ፡፡ ይህ ዘዴ የአከባቢን ሁኔታ ተረድቶ መልስ መስጠት የሚችል ነዉ፡፡ ዳሳሽ ማቴሪያሎች ብዙ ጊዜ ጥንቅር ማቴሪያሎች ናቸዉ፡፡ ጥንቅር ማቴሪያል ማለት ደግሞ ሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ ቁሶች የተሰራ ማቴሪያል ማለት ነዉ፡፡ እነዚህ ዳሳሽ ማቴሪያሎች ከተለመዱ የማቴሪያል አይነቶች በበለጠ መንገድ ጠቀሜታ ያላቸው ሲሆን የራሳቸው የሆነ የአከባቢዉን ሁኔታ መቆጣጠር የሚችሉበት ዘዴ አላቸው፡፡ ለመሳሌ ያህል ክብደታቸዉ አነስተኛ መሆን፡ በቀላሉ በዝገት የማይጠቁና የተሰሩበት መዋቅር ጠንካራና ሊቆይ የሚችል በመሆኑ ነዉ፡፡ ባለንበት 21ኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን ለብዙ አገልግሎት ይዉላሉ፡፡

በትራንስፖርቴሽን፡ ለምሳሌ በማይክሮ ኤሌክትሮኒክስ ክፍል ዉስጥ ሆኖ ክብደት ሲጫነዉ ከፍተኛ የሆነ መጠን ያለዉ ኤሌክትሪክ ሀይልን ማመንጨት

በአይሮፕላን ማምረቻ ፋብሪካ ዉስጥ፡ በተለይ በአሜረካ የአየር ሀይል ምርምር ማእከል፡የጦር ሰራዊት ምርምር ማእከል፡ በባህር ሀይል ምርምር ማእከልና ናሳ ዉስጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለዉ፡፡

በመኪን ማምረች ፋብሪካ ዉስጥ፡ በመኪና ማምረቻ ኢንዱስትሪ ዉስጥ ዳሳሽ ማቴሪያልን በከፍተኛ ሁኔታ እንጠቀማለን፡፡ ለምሳሌ በመኪና ማምረቻ ዘርፍ ዉስጥ በማይክሮ ኤሌክትሮ መካኒካል ሲስተም ዉስጥ እንደ ስሜት ተረጂ ክፍል ሆኖ በማገልገል ኤርባግንና አንቲ ሎክ የመኪና ማቆሚያ ዘዴዎችን ወደ ስራ ያሰማራል፡፡

በሰርጓጅ መርከብ ዉስጥ፡ በተለይ በኦፕቲክ ብራግ ግሬቲንግ ስሜት ተረጂ አማካኝነት የካርበንን ፋያበር ዉጥረት ለመለካት፡ በሰርጓጅ መርከብ ዉስጥ ሊፈጠር የሚችልን ከፍተኛ የሆነ ርግብግቢት ወይንም ድምጽን ለመቀነስ ያገለግላል፡፡

በባቡር ሀዲድ ላይ እንጠቀማለን፡ በሀዲድ ክፍል ላይ ኢንፍራሬድ ጨረርና የመኪና ፍጥነትን መለኪያ ስሜት ተረጂ ማቴሪያልን በመግጠም የመኪናና የድልድይ ግጭት መኖሩን ለማረጋገጥ ያስችለናል፡፡

 

ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረዉ በዚህ ዘመን ከፍተኛ የሆነ የዳሳሽ ማቴሪያል ተፈላጊነት በገቢያ ዉስጥ ይገኛል፡፡ የመኪና ማምረቻ፡ የአዉሮፕላን ማምረቻ፡ የሰርጓጅ መርከብና የመሳሰሉት ኢንዱስትሪዎች ዘመናዊ ዳሳሽ መሳሪያን በመጠቀም በዘርፉ ያለዉን የቴክኖሎጂ አቅም ማሳደግ ችለዋል፡፡

አሁንም ቢሆን በተለያየ የስራ ዘርፍች ላይ ምርምር በማድረግ የዳሳሽ ማቴሪያሎችን የበለጠ ተግባራዊነት መረዳት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ያህል በፒዞ ኤሌክትሪክ ፋይበር ጥንቅርና ቅርጻቸዉን በሚያስታዉሱ ፖሊመር ማቴሪያሎች ላይ በመመራመር የህክምናዉ ዘርፍ ማሳደግ ይቻላል፡፡

ምንጭ፡ FrontiersinPost Comments(0)

Leave a reply