...

ለምግብነት የሚውል ስጋን በቤተሙከራ ማበልጸግ

አዲስ የተገኘው ቀመር የቤተ ሙከራ  ስጋ ተፈጥሯዊ ጣዕምና መልክ እንዲኖረው እያስቻለ መሆኑ ተነገረ፡፡ ተመራማሪዎቹ ተፈጥሯዊውን የእንስሳት ስጋ መተካት የሚችልና ጣዕሙ ከሌሎች አማራጮች ለተፈጥሯዊው የእንስሳት ስጋ የቀረበ እንደሆነ ስለ ግኝታቸው አስረድተዋል፡፡

በምርምሩ ሂደት በቤተ ሙከራ የበለጸጉ የጡንቻ ህዋሳትና የስብ ህዋሳት በአንድ ላይ ሆነው የተለያዩ ደረጃዎችን አልፈዋል፡፡ ይህ ስልትም በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት የአካል ንቅለ ተከላ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ህዋሳትን ለማበልጸግ ጥቅም ላይ ከዋለው መንገድ የተቀመረ ነው፡፡

አሁን ላይ በተለያየ መጠን ሰው ሰራሽ ስጋውን እያመረቱ እንደሆነ የተናገሩት ተመራማሪዎቹ ሰዎች ከጤናቸውና ከፍላጎታቸው ጋር የተስማማ የስብ መጠን ያለውን ስጋ መሸመት የሚችሉበት እድል እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል፡፡

ወደ ዚህ ስራ እንዴት እንደገቡ ሲናገሩ ተመራማሪዎቹ ምንም እንኳን በአለማችን ላይ ያለው የስጋ ፍላጎት እየጨመረ ቢሄድም አቅርቦቱ የመቀነስ ችግር ውስጥ በመግባቱ ነው ብለዋል፡፡ ከእንስሳት እርባታ ጋር የተያያዘውን የስጋ አቅርቦት ብቻ ተማምኖ መቀመጥ አይገባም ስለዚህ እንደዚህ ያሉ አማራጫቾች መኖር አለባቸው ሲሉ አክለዋል፡፡

ምንጭ SciTechDailyPost Comments(0)

Leave a reply