...

10 አስፈላጊና ነፃ የዊንዶውስ 10 መተግበሪያዎች

በ2021 ስራዎችን ይበልጥ ሊቀላጥፉ የሚችሉ እና አዳዲስ የዘመኑ ገፅታዎችን ያካተቱ የኮምፒውተር መተግበሪያዎች ሊያስፈልጉን ይችላሉ፡፡ ታዲያ ከዚህ በታች የምትመለከቷቸው 10 መተግበሪያዎች አዳዲስ ገፅታዎችን በማከል በአዲሱ የፈረንጆቹ አመት ብዙ ተጠቃሚ ያፈራሉ ተብለው የሚጠበቁ ናቸው፡፡ መረጃውን ያስነበበው ቴክራደር እነዚህ ጠቃሚ መተግበሪያዎችን እንደሚከተለው አስቀምጧል፡-

1 TestDisk

ሜካኒካል የሆነው የመረጃ ማከማቻ በተለያዩ ምከንያቶች ብልሽት በሚያጋጥመው ወቅት መረጃችንን ለማዳን የሚያስችሉ መተግበሪያዎች እጅግ ይጠቅሙናል፡፡ TestDisk ይህን መረጃ የማዳን እና የመመለስ ስራ በሚገባ ለመከውን የሚያስችል መተግበሪያ ሲሆን በ2021 በ open-source ከተመዘገቡ ጠቃሚ መተግበሪያዎች አንዱ ነው፡፡

2 Cobian Backup

ይህ መተግበሪያ ፋይሎቻችንን እንደመጠባበቂያ ለማስቀመጥ ከሚረዱ ከፍተኛ አቅም ካላቸው ነፃ የባካፕ ፓኬጅ (free backup packages) ውስጥ በቀዳሚነት የሚቀመጥ ሲሆን በ2021 ብዙ ተጠቃሚዎች ይኖሩታል ተብሎ የሚታሰብ ጠቃሚ መተግበሪያ ነው፡፡

3 Tablacus File managers

ይህ የፋይል ማስተዳደሪያ እንደ ዊንደዎስ ኤክስፕሎረር ባሉ የፋይል ማስተዳደሪያዎች ላይ የልተጨመሩ እንደ tabs ያሉ አዲስ ገፅታዎችን ያካተተ ከመሆኑም ባለፈ የፋይል ማህደሮችን በምንፈልገው መልኩ ስድሮ ለማስቀመጥ እና የማይፈለጉ ፋይሎችን ደግሞ ዲሴብል ለማድረግ የሚረዳ ነው፡፡

4 CCleaner

ኮምፒውተራችንን ሊያጨናንቁ የሚችሉ አላስፈላጊ መረጃዎች ለማፅዳት እና ተመሳሳይ ፋይሎችን ለይቶ ለማጥፋት CCleaner እጅግ ጠቃሚ መተግበሪያ ነው፡፡ ይህ መተግበሪያ ረጅም እና አድካሚ የማጽዳት ሥራዎችን በአንድ ቦታ ሊሰራለን ከመቻሉም ባለፈ በፈጣን የማጣሪያ ሥርዓት ኮምፒውተራችንን በፍጥነት አንዲጓዝ የሚያደርግልን ነው፡፡

5 LibreOffice

በ2010 የተመሰረተው ይህ የመፃፊያ ስርዓት በየጊዜው በሚጨመሩለት አዳዲስ ገፅታዎች ይበልጥ እየተሻሻለ የመጣ እና አሁን ላይ በጣም ፈጣን ለአሳሰራ ምቹ ከሚባሉ የመፃፊያ ስርዓቶች በቀዳሚነት የሚመደብ ነው፡፡ LibreOffice ምንም ከማይከፈልባቸው ጠቃሚ open-source መተግበሪዎች ውስጥ ቀዳሚው ሲሆን በቀጣዮቹ አመታትም ብዙ ተጠቃሚዎች እንደሚኖሩት የሚገመት ነው፡፡

6 Notepad++

የትኛውንም የኮዲንግ ቋንቋዎች ተጠቅመን ኮድ ለመፃፍ እና የተለያዩ ስራዎችን ለማከናወን የሚያግዘን ይህ መተግበሪያ ከማይክሮሶፍት ዊንዶውስ Notepad ጋር እንዳማራጭ ልንጠቀመው እና እጅግ የበዙ ኮንቴክስችዋል ፎርማቶችን (contextual formatting) ያቀፈ ጠቃሚ መተግበሪያ ነው፡፡

ከእነዚህ መተግበሪያዎች በተጨማሪ ለቪዲዮ፣ ለምስል እና ለድምፅ ማቀናበሪ የሚያግዙ እጅግ አስፈላጊ መተግበሪያዎች መረጃውን ባስነበበው ቴክራደር እንዲሁ የተቀመጡ ሲሆን እነሱም ለምስል ማስተካከያ (Polarr)፣ ለድምፅ ማቀናበሪያ (Audacity እና Cakewalk) እንዲሁም ለቪዲዮ መስሪያ (Shotcut) በተከታይነት ተቀምጠዋል፡፡

ምንጭ፡ TechradarPost Comments(0)

Leave a reply