...

በስልክ ንግግር ወቅት አላስፈላጊ ድምፆችን የሚያስወግደው መተግበሪያ

ባለፈው አመት ኮቪድ-19 ይዞት በመጣው መዘዝ ምክንያት ብዙዎች ከቤታቸው ሆነው ስራዎችን እንዲያካሂዱ ተገደው ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ ከስራ ጋር የተያያዙ የመረጃ ልውውጦችን ለማካሄድ አንደ መደበኛ ስልክ፣ የቪዲዮ ኮንፈረንስ እና ሌሎች የመገናኛ ቴክኖሎጂዎች በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ ታዲያ በዚህ የግንኙነት ሂደት ውስጥ ብዙዎች ሲቸገሩበት የነበረው ጉዳይ ባሉበት አካባቢ በሚሰሙ አላስፈላጊ ድምፆች ወይም (noises) የስልክ ግንኙነታቸው ተደጋግሞ መቋረጡ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ብዙዎቻችን መደበኛ ስልክ በምንጠቀምበት ወቅትም በተደጋጋሚ የሚያጋጥመን ችግር ሲሆን አዲሱ መተግበሪያም ቀላል መፍትሄን ያበጀ ይመስላል፡፡

the Krisp noise cancelling app በሚል የተሰየመው ይህ መተግበሪያ በመላው አለም ከሚገኙ ቴሌኮሚዩተሮች ጋር በጋራ ለመስራት በመቻሉ በቤታቸው ሆነው የሚሰሩ ሰዎች በመተግበሪያው የጠራ የድምፅ ሲስተም ወይም (crystal-clear audio) አማካኝነት ቤቶቻቸውን ፀጥ ወዳለ የመሰብሰቢያ አዳራሽ  ለመቀየር ያስችላቸዋል፡፡ መተግበሪያው ከ800 በላይ በሚሆኑ አንደ ዙም፣ ስካይፒ እና ሚት ባሉ የመገናኛ መተግበሪያዎች ላይ መጠቀም የሚቻል ሲሆን በስልክ ንግግር ወቅት ከሁለቱም አካላት የሚሰሙ አዋኪ ድምፆችን ለይቶ ለማስወገድም የሚያስችል ነው፡፡

ይህ መተግበሪያ አላስፈላጊ ድምፆችን አጣርቶ ለማስወገድ የሚችለው በተገጠመለት ጥልቅ የነርቭ አውታረመረብ ወይም (Deep Neural Network) አማካኝነት ሲሆን ይህም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ስርዓት ውስጥ ውስብስብ ከሚባሉት ቴክኖሎጂዎች አንዱ ነው፡፡ መተግበሪያውን የሰሩት ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት አዲሱ መተግበሪያ ከሌሎች ተመሳሳይ ምርቶች የሚለይበት ዋና ምክንያት ከሚጠቀመው ውስብስብ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስርዓት በተጨማሪ 20 ሺህ ድምፆችን እና 50 ሺ ተናጋሪዎችን በአንድ ጊዜ ለመለየት በመቻሉ ነው ይላሉ፡፡ ይህ ደግሞ እስካሁን ከተሰሩት አላስፈላጊ ድምፅ ማስወገጃ (noise cancelling) ስርዓቶች በቀዳሚነት አንዲቀመጥ ያስቸላዋል፡፡

የመተግበሪያው የአሰራር ሂደት ለተጠቃሚዎች ብዙ አማራጮችን እንዲያገኙ የሚስችላቸው ሲሆን ከግላዊ ጥበቃ ጋር በተያያዘም ምንም አይነት ክፍትት እንዳይኖርበት ተደርጎ መሰራቱን  ባለሙያዎች ይገልፃሉ፡፡

ምንጭ፡ FuturismPost Comments(0)

Leave a reply