በአሁኑ ጊዜ ዓለም ወደ አንድ የኢንፎርሜሽን መረብ በመጣበት ወቅት መረጃ የሰው ልጆችን የእለት ከእለት ተግባራቸውን ሚለዋወጡበትና የሚግባቡበት መሳሪያ እየሆነ ከመጣ ውሎ አድሯል፡፡ በተለይ በኢኮኖሚ በጣም የበለፀጉ አገሮች የመረጃ አያያዝ ስርዓታቸውን በማሻሻል ዌብ ቤዝድ (Web based) የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት መረጃዎችን ስርዓት ባለው መልኩ በማደራጀትና በማሰራጨት ኦንላይን (Online) አገልግሎተ በመስጠት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ማቀላጠፍ ችለዋል፡፡
በዚህ የመረጃ ማከማቻ እና መያዣ ቴክኖሎጂዎች ጋር በተያያዘ በአሁኑ ጌዜ ብዙዎቻችን መረጃዎቻችንን የት እንደምናስቀምጥ ግልፅ ቢሆንም የመረጃ መያዣ ቴክኖሎጂ መቼ ተፈለሰፈ የሚለው ጉዳይ እጅግ አስገራሚ ትንታኔ የሚቀርበበት ጉዳይ ነው፡፡ አንዳንድ የዘርፉ ሳይንቲስቶች እኤአ ከ1890 አንስቶ የመረጃ መያዣ ቴክኖሎጂዎች እየተፈጠሩ መምጣቻውን የሚገልፁ ቢሆንም አብዛኞቹ የሚስማሙበት ግን ከ1930ዎቹ በኋላ መፈልሰፋቸውን ነው፡፡
የመረጃ መያዣ መሳሪያዎች አሁን ላይ ከደረሱበት እጅግ የተራቀቀ የቴክኖሎጂ ደረጃ በፊት ቀደም ባሉት ጊዜያት እጅግ ረዥም የፈጠራ ሂደቶችን ያሳለፉ ሲሆን ይህን አስገራሚ የቴክኖሎጂ ሂደት ከ1930ቹ እስከ 80ዎቹ እንደሚከተለው ማስቀመጥ ይቻላል፡፡
1 Magnetic Drum
ይህ የመረጃ ማስቀመጫ መሳሪያ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት እኤአ በ1932 የተፈጠረና ከመጀመሪያው እጅግ በጣም ተሻሽሎ የመጣ ሲሆን ይህም 48KB መረጃዎችን በአምስት ከፋፍሎ ወርድ ዶክመንት (.Doc file) ማስቀመጥ ተችሎ ነበር፡፡
2 Williams-Kilburn Tube
ይህ የመረጃ መስቀመጫ መሳሪያ እኤአ በ1947 የተሰራ ቴክኖሎጂ ሲሆን የመጀመሪያው RAM (Randem Access memory) ነው:: የመጀመሪያው ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ምስሎችን ለማስቀመጥ ያስቻለም ነበር፡፡ ይህም እስከ 0.128KB የሚሆኑ ምስል ፋይሎችን ለማስቀመጥ አስችሏል፡፡
3 Magnetic Tape Drive
ይህ የመረጃ ማስቀመጫ ቴክኖሎጂ በጀርመን ሀገር የተፈጠረ ቢሆንም እጅግ በጣም አስደናቂ በሆነ መልክኩ ተሻሽሎ አገልግሎት ላይ የዋለው ግን እኤአ በ1951 ሲሆን በአንድ ላይ እስከ 23 የሚሆኑ የWord Doc እና 10 PDF ፋይሎችን እና ሙዚቃ ሪከርድ አድርጎ እስከ 230KB የሚደርስ መረጃ በማስቀመጥ ነበር የጀመረው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ቢመጣም እስካሁን ድረስ መረጃዎችን ለማስቀመጥ እንጠቀምበታለን፡፡
4 Magnetic Core
ይህም ቴክኖሎጂ በተመሳሳይ አመት 1951 በአሜሪካ MIT Whirlwind computer የተፈጠረ ሲሆን እስከ 2000 ቴክስት ካራክተሮችን የመያዝ አቅም የነበረው ሲሆን ኮምፒውተር ላይ ተገጥሞም አገልግሎች መስጠት ችሏል፡፡ እስከ 1975 ድረስ በተለያዬ መስክ አገልግሎት ሲሰጥ ነበር፡፡
5 Hard Disk Drive (HDD)
ይህ የመረጃ ማስቀመጫ መሳሪያ በመጀመሪያ በአይቢኤም በ1956 የተሰራ ሲሆን 3,750KB ወይም 3.75 MB ያህል መረጃ የማስቀመጥ አቅም ነበረው፡፡ ይህም መሳሪያ 45 ደቂቃ ርዝማኔ ያለው ቪዲዮ ወይም 5ሚሊዮን ካራክተር ያለው ቴክስት ፋይሎችን ማስቀመጥ ያስችል ነበር፡፡
6 Floppy Disk
ይህም የመረጃ ማስቀመጫ መሳሪያ በመጀመሪያ በአይቢኤም በ1967 የተሰራ ሁኖ 8 ኢንች ርዝማኔ ያለው ሲሆን ምስሎችን (images) እና 8 ወርድ ፋይሎችን ለማስቀመጥ ያገለግል የነበረ ሲሆን በ1978 ከ10 በላይ ድርጅቶች ለአጠቃቀም ቀላልና ተንቀሳቃሽ በሆነ መልኩ 3.5 ኢንች በማደረግ ለገበያ አቅርበውት ነበር፡፡ የሚገርመው ግን ይህን መሳሪያ ከገበያ የጠፋ ቢሆንም እስከ ዛሬ ድረስ በአሜሪካ በኒውክለር የምርምር ሂደቶች ውስጥ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
8. Compact Disc (CD)
እኤአ በ1982 በሶኒ እና ፒሊፕስ የተሰራ ሲሆን ከ650-700MB መረጃ የመያዝ አቅም ያለው ቢሆንም ሰባ ሺ (70 000) ዶክመንት ካራክተር ፋይሎችን ወይም አንድ መቶ አርባ (140) ደቂቃ ቪዲዮ የማስቀመጥ አቅም ነበረው፡፡ በ1980ዎች በብዛት በሙዚቃውና ፊልም ኢንደስትሪው ዘርፍ በብዛት አገልግሎት ላይ የዋለ ሲሆን የተጠቃሚዎች ቁጥር ከቴክኖሎጂው መስፋፋት ጋር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ቢመጣም አሁንም ገበያ ላይ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
ምንጭ Frontierinternet እና Big Think
Post Comments(0)