...

ዲ ኤን ኤ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲንቀሳቀስ የሚያሳይ ምስል በተመራማሪዎች ይፋ ተደርጓል

ዲ ኤን ኤ ወይም ዘረመል የምንለው የሞሎኪውል ስብስብ በህዋሶቻችን ውስጥ የሚያደርገውን የመተጣጠፍ ወይም ዳንስ መሰል እንቅስቃሴ የሚያሳይ የመጀመሪያ ምስል ከሰሞኑ በተመራማሪዎች ይፋ ተደርጓል፡፡ እንግሊዝ ውስጥ በሚገኙ ሶስት ዩኒቨርስቲዎች በጥምረት የተሰራው አዲሱ ምርምር ተመራማሪዎች ጥቅም ላይ ባዋሉት እጅግ የላቀ የአቶሚክ ኃይል ማይክሮስኮፕ እና ምስል ለመከሰት በሚያስችል የሱፐር ኮምፒውተር ሲሚዩሌሽን አማካኝነት የተሰራ ነው፡፡

ከፀጉር ቀለማችን አንስቶ እስከ እግር ጥፍራችን ድረስ በምን ልክ ሰውነታችን እንደሚያድግ የሚወስነው እና ትእዛዝ የሚሰጠው ይህ የሰው ልጅ የዘረመል ኮድ (DNA) አጠቃላይ ለመኖራችን ምከንያት የሆነውን ፕሮቲን በማበልፀግና በማምረትም ሰውነታችን በትክክል ስራውን እንዲሰራ የሚያደርግ ረቂቅ የተፈጥሮ ስራ ነው፡፡ እንደአውሮፓውያን አቆጣጠር በ1953 ጀምስ ዋትሰን እና ፍራንሲስ ክሪክ በተባሉ የስነ ህይወት ተመራማሪዎች የመጀመሪው የዲ ኤን ኤ ድርብ-ሄሊክስ መዋቅር (double-helix structure) ይፋ ከተደረገ በኋላ፤ እነዚህ ዘረመሎች በህዋሶቻችን ውስጥ የሚደርጉት የመተጣጠፍ እንቅስቃሴን ምን እንደሚመስል የሚያሳየው አዲሱ የተመራማሪዎች ምስል ከ70 አመታት በኋላ በዲ ኤን ኤ ዘሪያ የተገኝ ትልቅ የምርምር ውጤት ይሆናል፡፡

ተመራመሪዎች የማይታመነውን ባለነጠላ የዲ ኤን ኤ ሞለኪውል የምስል እንቅስቃሴ ለማበልፀግ በማይክሮስኮፑ የወሰዱት እጅግ ከፍተኛ ጥራት ያለው የምስል ቀረፃ በእጅጉ የረዳቸው ሲሆን ከዚህ በፊት በነበረው የቴክኖሎጂ አቅም የዲ ኤን ኤ ምስል መውሰድ ቢቻልም እንደአሁኑ ሲንቀሳቀስ የሚያሳይ ምስል ግን ማግኘት አልተቻለም ነበር፡፡

ይህ ተንቀሳቃሽ ምስል የዲ ኤን ኤ ድርብ-ሄሊክስ መዋቅር ውስጥ ያሉ እያንዳንዱን የአቶም አቀማመጥ በማሳየት ሁሉም ሞለኪውሎች በህዋሶቻችን ውስጥ የሚኖራቸውን የመዟዟር እና የመጠማዘዝ እንቅስቃሴ ለማብራራት ያግዛል፡፡ የዘረመሉን ተንቀሳቃሽ ምስል በማበልፀግ ሂደት ውስጥ ዋና ተሳታፊ የነበሩት ዶ/ር አሊስ ፓይን ይህ የምርምር ውጤት አጠቃላይ በዲ ኤን ኤ ዘሪያ የሚኖረንን የእውቀት አድማስ ለማስፋትና ሌሎች አደዲስ ግኝቶችን ለመጨምር ከማገዙም ባላይ አሁን ባለው ህክምና ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ለማከል እንደሚረዳም ይናገራሉ፡፡

ምንጭ፡ Express እና BigthinkPost Comments(0)

Leave a reply