...

የአጋላጩ መረጃ የቦይንግ ኦክስጅን አቅርቦት ላይ ጥያቄ አስነሳ

የቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን በጉዞ ላይ ሳለ አደጋ ቢደርስ ተጓዦች ኦክስጅን ላያገኙ እንደሚችሉ አንድ የድርጅቱ የቀድሞ ሠራተኛ አጋለጠ። ጆን ባርኔት የተባለው ግለሰብ የሠራው ጥናት፤ አውሮፕላኑ ውስጥ በአደጋ ጊዜ ኦክስጅን የሚያሰራጨው መሣሪያ የተበላሸ ወይም የማይሠራ መሆኑን እንዳሳየው ይፋ አድርጓል። በአንድ የቦይንግ ማምረቻ ፋብሪካ ውስጥ ሆን ተብሎ የማይሠሩ መሣሪያዎች እንደሚገጠሙም አጋላጩ ተናግሯል።

...

ቻይና ጌም በሚያዘወትሩ ታዳጊዎች ላይ ሰዓት እላፊ ጣለች

ቻይና በይነ-መረብ ላይ ተተክለው 'የቪድዮ ጌም' ሲጫወቱ የሚውሉ ታዳጊዎች ላይ እግድ ጥላለች። ከ18 ዓመት በታች ያሉ 'ኦንላይን ጌመኞች' ከዚህ በኋላ ከምሽቱ 4 ሰዓት ጀምሮ እስከ ጠዋት ሁለት ሰዓት ድረስ መጫወት አይችሉም ተብሏል። አልፎም በሥራ ቀናት 90 ደቂቃ፤ ቅዳሜ እና እሁድ ደግሞ ለ3 ሰዓታት ነው መጫወት የሚፈቀድላቸው። የቻይና ባለሥልጣናት፤ የበይነ-መረብ ቪድዮ ጌሞች ሱስ እየሆኑ ነው፤ ትውልዱንም ጤና እየነሱት ነው በሚል ነው ይህን ሕግ ያወጡት።

...

የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ እና አውሮፓ አዕምሮአዊ ንብረት ፅህፈት ቤቶች ጋራ በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ

የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ የአዕምሮ ንብረት ድርጅት እና የአውሮፓ አዕምሮ ንብረት ፅህፈት ቤት ጋራ በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡

...

የፈጠራ ባለሙያዎች ስራዎቻቸው ፍሬ የሚያፈራበት ፕላትፎርም ለመፍጠር እንደሚሰራ ተገለፀ

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት በዛሬው ዕለት ያዘጋጀውና ዋና ትኩረቱን ሃገራዊ በሆኑ የፈጠራ ፕሮጀክቶች ላይ ያደረገው የአንድ ቀን ወርክሾፕ ተካሂዷል፡፡ በመድረኩ ከተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት የተወጣጡ ተመራማሪዎች፣ ቴክኖሎጂስቶች እና የፈጠራ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በኢኖቬሽን ዘርፍ ላይ የሚታዩ ችግሮችን እና ሊወሰዱ የሚገቡ የመፍትሄ ሃሳቦች ላይ ጥልቅ ውይይት ተደርጓል፡፡