...

የኢኒስቲትዩቱ ሰራተኞች በተለያዩ ቦታዎች በመገኘት ልዩ ልዩ ድጋፎችን አድረገዋል

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ሰራተኞች በኮልፌ ቀራኖዮ በሚገኙ ረዳት የሌላቸው አረጋውያን መኖሪያ ቤቶች በመገኘት ልዩ ልዩ ድጋፎችን አድርገዋል፡፡ የተቋሙ ሰራተኞች ይህን ድጋፍ ያደረገት በአካባበቢው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እየሰጠ ከሚገኘው ባይሽ ኮልፌ የአረጋውያን መርጃ ማህበር ጋር በመተባበር ሲሆን፤ በአካባበዊ ለሚገኙ ረዳት የሌላቸው አረጋውያንም የዘይት፣ የዱቄት እና ሌሎች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳ ቁሶችን ድጋፍ አድረገዋል፡፡

የኢኒስቲትዩቱ ሰራተኞች ሲዳርታ በሚባለው የህፃናት ማሳደጊያ ማዕከል በነበራቸው ጉብኘትም ለህፃናቱ እና ለአሳዳጊዎች የሚሆን በየኢኒስቲትዩቱ የተሰራ የፊት መሸፈኛ ጭብል እና የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር ለማዕከሉ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ሰራታኞች ይህን ድጋፍ ያደረጉት የማህበረሰብ አቀፍ ስራዎችን በሚያከናውነው የሶሻል ኮሚቴ አማካኝነት ሲሆን፤ ድጋፉም ኮሚቴው ከሚሰራቸው መሰል ተግባራት ውስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው፡፡

 

 

 Post Comments(0)

Leave a reply