...

የራዲዮ ሞገድ ግንኙነቷ ለረዥም ግዜ የተቋረጠው ፓዮኔር 10

በፈረንጆቹ ማርች 2 ቀን 1972 ዓ.ም በአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቁዋም ናሳ ሰራሽነት ከምድራችን የመጠቀችው ፓዮኔር 10 የተሰኘችዋ አሳሽ መንኮራኩር (space probe) በፕላኔት ማርስ እና ጁፒተር መሀከል ሰፍሮ የሚገኘውን እና የአስትሮይዶች ክምችት እንደሆነ የሚታመነውን ግዙፉን 'የአስትሮይድ ቀበቶ (Astroid belt) በማለፍ እስከዛሬ ከመጠቁት አሳሽ መንኮራኩሮች ሁሉ በቀደምትነት የተቀመጠች ሲሆን የፕላኔት ጁፒተርንም ገፅታ ለመጀመርያ ግዜ ከቅርበት ፎቶ በማንሳት ያሳየችን መንኮራኩር ናት።

በዲሴምበር 3 ቀን 1973 ዓ.ም ከምድር ከመጠቀች ከ1 ዓመት ከ8 ወር በሁዋላ ግዙፏ ፕላኔት ጁፒተር ጋር በመድረስ በዋነኝነት ከአሞኒያ ጋዝ ከተሰራው የፕላኔቷ ዳመና በ130,000 ኪ.ሜ ከፍታ ላይ በመሆን አስደናቂ ፎቶዎችን በማንሳት ወደ ምድር ልካለች። ከዚህ በተጨማሪ የጁፒተርን ከባቢ መግነጢስ (magnetosphere)፣ የጨረራ ቀበቶ (radiation belt)፣ መግነጢሳዊ መስክ (magnetic field)፣ እና ከባቢ አየራዊ ስሪት (Atmospheric content) በማጥናት ከሷ በማስከተል ለመጠቁት ለእነ ቮዬጀር እና ጋሊሊዮ ለመሳሰሉት አሳሽ መንኮራኩሮች ወሳኝ መንገድ ቀይሳ አልፋለች።

እንደአውሮፓውያኑ በመጋቢት 31 ቀን 1997ዓ.ም ከምድር ከመጠቀች ከ25 ዓመታት በሁዋላ ከምድር ካላት ርቀት አንፃር የምትልከው ሲግናል ሊቋረጥ የቻለው Pioneer 10 አሳሽ መንኮራኩር ወደ ግዙፏ ፕላኔት ጁፒተር ለመጀመሪያ ጊዜ መደርስ የቻለች የስፔስ ፕሮብ ስትሆን በአጠቃላይ 258 ኪሎ ግራም በመመዘን መጠን የለሹን የህዋ ክፍል በማሰስ ላይ ትገኛለች። በሴኮንድ 12 ኪ.ሜ በሆነ ፍጥነት ጥልቁን ህዋ እየሰነጠቀች ዛሬም ጉዞዋን እንደቀጠለች የሚታሰበው ፖዮኔር 10 አሁን ላይ ከምድራችን ከ16 ቢልዮን ኪሎሜትሮች በላይ ርቃ እንደምትገኝ ይታመናል። ከሷ በሁዋላ እንደመጠቁት እንደ መንትያዎቹ ቮዬጀር አሳሽ መንኮራኩሮች ሁላ ፓዮኔር 10ም በውስጧ ምድራችንን የሚገልፅ እና መገኛ አቅጣጫዋን የሚጠቁም ካርታ ይዛለች።

ይህች አሳሽ መንኮራኩር ማረፊያዋ በውል አይታወቅምና ምናልባት ከኛ ውጭ ህይወት ያላቸው ፍጡራን ይህችን መንኮራኩር ቢያገኟት ከየት እንደመጣች እና ስለመጣችበት ፕላኔት በደምብ የሚያስረዳ ካርታ እና ስእላዊ መግለጫን ያገኛሉ። ፓዮኔር 10 በዚህ ፍጥነት እየገሰገሰች 'አልደባርያን' ወደተሰኘው ግዙፍ ቀይ ኮከብ አቅጣጫ በመጉዋዝ ላይ እንደምትገኝ የሚታመን ሲሆን ኮከቡ ጋር ለመድረስ ከ1 ሚልዮን አመታት በላይ ሊፈጅባት እንደሚችል ይታሰባል። ምንጭ፡ Airtable universe እና Big ThinkPost Comments(0)

Leave a reply