...

በሁለት አመት ውስጥ የአየር ታክሲ አገልግሎት ለመስጠት ያቀደው ቮሎኮፕተር

ብሩስኩል በተባለቸው የጀርመን ከተማ እንደአውሮፓውያኑ በ2011 የተመሰረተው የቮሎኮፕተር ኩባንያ የአየር ላይ ታክሲዎችን በማምረት ለርዥም ጊዜ የሙከራ በረራዎችን ሲያካሂድ የቆየ ደርጅት ነው፡፡ በጀርመን መቀመጫውን ያደረገው ይህ ኩባንያ በቅርቡ አካሄድኩት ባለው የካፒታል ማሻሻያና ማስፋፊያ ፕሮግራም በጥቅሉ 322 ዩሮ ገቢ በማሰባሰብ በ2020 ለእይታ ያበቃትን ቮሎሲቲ (VoloCity) የተሰኘች የአየር ታክሲ ወደተሟላ አገልግሎት ለማምጣት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡

በከተሞች በሚደረግ የአየር በረራ ወይም (UAM) ኢንዱስትሪ ላይ በቀዳሚነት የሚገኘው ቮሎኮፕተር በቀጣዮቹ ሁለት አመታት ውስጥ የመጀመሪያውን የአየር ታክሲ አገልግሎት ለማቅረብ የሚስችለውን ዝግጅት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በቅርብ አመታት ውስጥ በሄልሲንኪ፣ ስቱትጋርት፣ ዱባይ እና የሲንጋፖር ከተማዎች ላይ የበረራ ሙከራዎችን ሲያደርግ የነበረው ኩባንያው በቀጣዮቹ አመታት መደበኛውን የአየር ላይ የታክሲ አገልግሎት በአሜሪካ፣ በእስያ እና በአውሮፓ ለመጀመር በመንቀሰቃስ ላይ ነው፡፡

ቮሎኮፕተር ከየትኛውም የአየር ታክሲ ኩባንያዎች በበለጠ በተለያዩ የአለማችን ከተሞች ከ1,000 በላይ የሙከራ በረራዎችን አከናውኗል የሚሉት የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሎሪያን ሮይትር በ2023 አምስተኛ ትውልድ በሆነችው ቮሎሲቲ አማካኝነት የመጀመሪያውን የኤሌክትሪክ የአየር ታክሲ አገልግሎት ለማካሄድም በመንገድ ላይ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ ኩባንያው ለንግድ የሚያቀርባቸው በራሪ የታከስሲ ሞዴሎች ቮሎሲቲ እና ቮሎድሮን የተባሉት የቮሎኮፕተር ምርቶች ሲሆኑ ቮሎሲቲ የተባለችው ሞዴል በትልልቅ ከተሞች የመንገደኛ መጓጓዣ አገልግሎት እንደምትሰጥ የተነገረ ሲሆን ቮሎድሮን የተባለቸውም ሞዴል ደግሞ የእቃ ማጓጓዣ አገልግሎት እንደምትሰጥ ተገልጿል፡፡

በአለማችን ላይ በዚህ የአየር ታክሲ አገልግሎት ዘርፍ ውስጥ እንደ ኤርባስ እና ሃዩንዳይ ያሉ ትልልቅ ድርጅቶች የሚንቀሳቀሱ ሲሆን የመጀመሪያውን የንግድ የአየር ታክሲ አገልግሎት ላመቅረብም በመፎካከር ላይ ይገኛሉ፡፡

ምንጭ፡ InceptivemindPost Comments(0)

Leave a reply