...

ከ USB አስር እጥፍ የሚፈጥን የመረጃ ማስተላለፊያ ግኝት

ተመራማሪዎች መረጃን በከፍተኛ ፍጥነት ማስተላለፍ የሚያስችል ስልትን ማበልጸጋቸው ተሰማ፡፡ ይህ የመረጃ ማስተላለፊያ ዘዴ ከመደበኛው የመረጃ ማስተላለፊያ ዘዴ አስር እጥፍ እንደሚፈጥን የተነገረለት ሲሆን በመረጃ ቋቶች አካባቢ የሚስተዋለውን የኃይል ፍላጎትም እንደሚያሻሽለው ተሰምቷል፡፡ በተጨማሪም ከፍኛ ፍሪኩየንሲ የሲልከን ቺፕ አና የፖሊመር ገመዶችን ይጠቀማል፡፡

ከርቀት ሆኖ የተለያዩ ስራዎችን መስራት እየተለመደ በመጣበት በዚህ ዘመን ፈጣን የመረጃ ማስተላለፊያ ዘዴዎች መኖራቸው እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በኮምፒውተር ቺፖች፣ ክላውድ ኮምፒውቲንግ፣ ኢንተርኔት እና በመሳሰሉት ከፍተኛ የሆነ የመረጃ መተላለፍ ሂደት አለ፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው ደግሞ በተለመደው የኮፐር ሽቦ ወይም ገመድ አማካኝነት ነው፡፡ እንደ USB እና HDMI ባሉ መረጃ ማስተላለፊያዎች ውስጥ የሚገኘው የኮፐር ሽቦ ከፍተኛ መጠን ያላቸውን መረጃዎች በሚያስተላልፉ ጊዜ ከፍ ያለ የኃይል ፍልጎት አላቸው፡፡ በሚባክነው ኃይልና በሚተላለፈው መረጃ መካከል አለመመጣጠን አለ፡፡

በአሁኑ ሰዓት የመረጃ በፍጥነት መተላለፍ ፍላጎት በሴኮንድ 100 ጌጋ ባይት ድረስ እያደገ ቢሆንም የመረጃ ማስተላለፊያ መንገዱ ግን አሁንም ረጃጅም የኮፐር ገመዶችን በመጠቀም ነው፡፡ ከኮፐር ገመዶች ውጭ ሌላኛው አማራጭ የመረጃ ማስተላለፊያ ፋይበር ኦፕቲክ ገመድ ሲሆን እሱም ቢሆን የራሱ የሆኑ ውስንነቶች ያሉበት ነው፡፡ ይህ ፎቶኖችን የሚጠቀመው የመረጃ ማስተላለፊያ ቁስ መረጃን በፍጥነትና በቀላል ኃይል የሚያስተላልፍ ቢሆንም የሲልከን ኮምፒውተር ቺፖች ፎቶኖችን ለመጠቀም አያስችሉም፡፡ በአሁኑ ሰዓት የፋይበር ኦፕቲክስ መረጃ ማስተላለፊያ መንገድ የሆኑትን ፎቶኖች በሲልከን እንዲሰሩ የማድረጊያ ዘዴዎች የሉም፡፡ እነዚህና መሰል ችግሮች መኖራቸው ተመራማሪዎች ሌላ ፈጣንና ኃይል ቆጣቢ የሆነ መንገድን እንዲያስቡ አስገድዷቸዋል፡፡

የምርምር ቡድኑም በኮፐር እና በፋይበር ገመዶች የሚስተዋሉ ችግሮችን በማሻሻል አዲስ ስልትን ማበልጸጉን ተናግሯል፡፡ አዲሱ ግኝት በፕላስቲክ ፖሊመር የተሰራ በመሆኑና እጅግ ቀላልና ከተለመዱ ገመዶች በተቃራኒው በቀላል ወጭ መመረት የሚችል ነው፡፡ እንዲሁም ግኝቱ ያለተጨማሪ ግብዓት ከሲልከን ቺፖች ጋር ተዋህዶ መስራት የሚችል ነው፡፡

ምንጭ SciTechDailyPost Comments(0)

Leave a reply