...

የሮቦት ቴክኖሎጂ በግብርናው ዘርፍ

በ2050 የዓለም ህዝብ ብዛት ከ 9 ቢሊየን በላይ እንደሚሆን ሲገመት በተመሳሳይ ሁኔታ መሬት እየጠበበች መምጣት ሕዝቡን በበቂ ሁኔታ መመገብ በጣም አስቸጋሪያ ደርገዋል፡፡ ወደ ፊት ይህን ሕዝብ እንዴት መመገብ ይችላል የሚለውን ትልቁን እና አሳሳቢ የዓለማችን ጥያቄ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ በመሆኑም ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም አማራጭ የሌለው ሲሆን ከነዚህም ቴክኖሎጂዎች መካከል ሮቦቶች ቀዳሚውን ቦታ ይይዛሉ፡፡

ይህን ችግር ለመቅረፍ ሲባል ብዙ ሀገሮች ቀድሞ ከነበራቸው ቴክኖሎጂን መሰረት ካደረገ የአመራረት ሂደት በተጨማሪ ሮቦቶችን በመጠቀም የተሸለ የአመራረት ስልት በመጠቀም አጥጋቢ ውጤት ማስመዝገብ ጀምረዋል፡፡  ከዚህም ባለፈ ይህ ቴክኖሎጂ አርሶ አደሮች የአየር ትንበያን በመከታተል በወቅቱ አዝመራቸውን እንዲዘሩ እና እንዲሰበስቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት በመሆኑ ዘርፈን በሚፈለገው መጠን ለማዘመን እና ለማሳደግ ትልቅ እድል ይፈጠራል፡፡

ቴክኖሎጂዎችን በግብርና እና ባለሙያዎችን በስፋት በማስተዋወቅ ስራ በመስራት ባላቸው ውስን መሬቶች ላይ ብዙ መስራት እንዲችሉ ከማድረግም በላይ የተፈጥሮ ዝናብን በመጠበቅ ላይ የተመሰረተውን የግብርና ስልት ምርታችንን በአፋጣኝ እንዲሻሻል እና በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች ገቢ ብሎም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እንዲያድግ ማድረግ ይቻላል፡፡ ለግብርና የሚያገለግሉትን የሮቦት ሲስተሞችን በመጠቀም የከርሰ ምድር ውሃን ያለበትን ለይተው እንዲቆፍሩ፣ ጊዜውን ጠብቀው መሳሪያዎች ላይ ውሃም ሆነ ማዳበሪያ እንዲረጩ የሚያደርጉ እና የመሳሰሉትን አድካሚ የሰው ጉልበት የሚጠይቁ የግብርና ስራዎችን በአጭር ጊዜ እንዲያከናውኑ በማድረግ የአርሶ አደሮችን ምርታማነት እና  ውጤታማነት ማሳደግ ይቻላል፡፡

ከላይ ከተጠቀሱት ከብዙ በጥቂቱ ሲሆኑ ከነዚህም በተጨማሪ የማዕድን ቁፋሮ፣ ወታደራዊ አገልግሎት፣ በትልልቅ ኢንዱስትሪዎች፣ በሌሎች የህዋ ሳይንስ ጥናት ዘርፎች ዙሪያ እና ሌሎች አስቸጋሪ እና ፈታኝ ስራዎችን ከላይ የሮቦት ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም በብዙ የስራ ዘርፎች ላይ የተሻለ ዕድገት እንዲመጣ የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ማድረግ ይቻላል፡፡

ምንጭ፡ growingworld24Post Comments(0)

Leave a reply