...

ለኤሌክትሪክ መኪኖች ባትሪን በ5 ደቂቃ መሙላት የሚያስችል ቴክኖሎጂ

የኤሌክትሪክ መኪኖችን ባትሪ በ5 ደቂቃ ውስጥ መሙላት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ስቶር ዶት በተሰኘ አንድ ድርጅት ቀረበ፡፡ ይህ ከወደ እስራኤል የተሰማው መረጃ ሬንጅ አንዛይቲ በመባል የሚታወቀውን የሐይል ማጣት ፍራቻን እደሚቀንስ ተገልጧል፡፡ ይህ በጣም በፍጥነት የመሙላት አቅም ያላቸውን ባትሪዎች በመስራት የሚታወቀው ስታርትአፕ ኩባንያ ስቶርዶት ፈጠራ የሆነው ባትሪ የመጀመሪያ ትውልድ የሊቲየም አዮን ባትሪ ነው፡፡

ፈጠራው የኤሌክትሪክ መኪናዎችን ባትሪ ለመሙላት የሚያፈልገውን ጊዜ በእጅጉ መቀነስ የሚያስችል ፈጠራ ሲሆን በአምራቾች በመቶዎች የሚቆጠሩ የመጀመሪያ ደረጃ ምርቶች ሙከራ ተደርጎባቸዋል፡፡ ይህ አድራሻውን ቴላቪቭ አቅራቢያ ያደረገው ኩባንያ በ2012 የተቋቋመ ሲሆን አራት የተለያዩ ባለሀብት ድርጅቶችን በማቀፍ ስራውን እየሰራ ነው፡፡ ለመነሻም ባትሪውን በስልኮች፣ በድሮኖችና በስኩተሮች ላይ መሞከሩን ተናግሯል፡፡

እንደሚታወቀው በ2019 በተደረገው የኖቤል ሽልማት አሜሪካዊው ጆን ጉድኢናፍ እና ስታንሊ ዋይቲንግሃም በኬሚስትሪ ዘርፍ የሊቲየም አዮን ባትሪን በመስራታቸው ምክንያት ተሸልመዋል፡፡ በወቅቱም ይህ ባትሪ ከሞባይል ስልክ እስከ መኪና ድረስ ላሉ ሃይል ለሚፈልጉ መገልገያዎች እንደሚውል ተገልጦ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በፍጥነት ወይም በ5 ደቂቃ ውስጥ ሀይል መሙላት የሽልማቱ አካል እንዳልነበረ ተመራማሪዎቹ አስታውሰዋል፡፡

ምንጭ Tech Xplore  Post Comments(0)

Leave a reply